በጅግጅጋ እስር ቤት ጄይል ኦጋዴን በደል ሲፈጸምባቸው የነበሩ ዜጎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተጠየቀ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/176215

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በቀድሞ የሶማሊ ክልል አስተዳደር ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አንዲደረግላቸው ጠየቀ።
No photo description available.ግንባሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የቀድሞ የክልሉ አስተዳድር ዜጎችን የኦብነግ ታጋዮች ቤተሰቦች ናችሁ፣አባል እና ደጋፊ ናችሁ በሚል የተለያዩ በደል ሲፈጸምባቸው ነበር ብሏል።
እነዚህ ዜጎች ማስረጃ በህገወጥ መንገድ በክልሉ እና በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ እስር ቤቶች አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች እንደደረሰባቸው ግምባሩ ገልጿል።

በተለይም በጅግጅጋ በሚገኘው እስር ቤት በተለምዶ ጄይል ኦጋዴን በሚባለው እስር ቤት ከኦብነግ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ዜጎች ይገረፉ፣አካላቸው ይቆረጥ ነበር ብሏል።
በእስር ቤት የነበሩ እነዚህ ዜጎች በአገር አቀፍ ደረጃ በመጣው ለውጥ ሳቢያ ከአሰር ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ቢቀላቀሉም በእስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ለካንሰር፣ለፊስቱላ እና ለአዕምሮ ህመም መጋለጣቸውን የኦብነግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሀሊሳ መሀዲ ተናግረዋል።
ከእስር ከተለቀቁት ወስጥ ሁለት ዜጎች በደረሰባቸው ከፍተኛ ስቃይ ህይወታቸው ማለፉም ተገልጿል።
ኦብነግ እነዚህን ተጎጂዎች በጂግጂጋ በአንድ ማዕከል ውስጥ ቢያሰባስባቸውም አፋጣኝ የህክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡
ወደ ማዕከሉ ከገቡ ዜጎች ወስጥ በቶርቸር የተጎዱ ፤ ግማሽ አካላቸውን ያጡ ተጨማሪ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚፈልጉ እንዲሁም ወደ ውጭ ሄደው መታከም ያለባቸው ቢሆንም ድጋፍ የሚያደርግላቸው ተቋም ጠፍቶ ለከፋ የጤና እንግልት መዳረጋቸውን ወይዘሮ ሃሊሳ ገልጸዋል።
በምንችለው አቅም እያሳከምናቸው እና እየቀለብናቸው እንገኛለን የሚሉት ወ/ሮ ሀሊሳ ድጋፍ ባለማግኘታችን ነገሩ ከእኛ አቅም በላይ ሆኗል ይላሉ፡፡
ቤተሰብ ያላቸውን ወደ ቤተሰባቸው እንዲሄዱ እና እዛ ተጠግተው እንዲኖሩ እያደረግን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.