በጅግጅጋ ጉምሩክ ናፍጣና ነዳጅን ጨምሮ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ የኮንትሮባንድ እቃ ከሃገር ሊወጣና ሊገባ ሲል ተያዘ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/74435

ባለፈው ህዳር ወር ብቻ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ናፍጣና ነዳጅን ጨምሮ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ የኮንትሮባንድ እቃ ከሃገር ሊወጣና ሊገባ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስትር ተናገረ፡፡
201 ሺህ ዶላርም በህገ-ወጥ መንገድ ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏልም ብሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ በላከልን መረጃ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ከተያዙ መካከል ከ4.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የቁም እንስሳት ይገኙበታል፡፡

በውጭ ምንዛሬ ተገዝተው የገቡ እንደ ናፍጣና ነዳጅ እንዲሁም የድንጋይ ከሰል ማዕድንም በህገወጥ መንገድ ከሃገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ውለዋል መባሉን ሰምተናል፡፡
በህገወጥ መንገድ ወደ አገር ሊገቡ ሲሉ ከተያዙት መካከል ደግሞ ፈዋሽና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ መድሃኒቶች፣ የታሸጉ ምግቦች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
Sheger FM

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.