በጉባ ወረዳ አለመረጋጋት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 121 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ የብሔር ግጭትና አለመረጋጋት ለመፍጠር አልሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ቡድን አካል ናቸው የተባሉ 121 ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ ሀምደኒል እንዳስታወቁት የጥፋት ቡድኑ በጦር መሳሪያ በመታገዝ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት 2፡30 አካባቢ በጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ የ13 ንጹኃን ዜጎችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ ቡድኑ የብሔር ግጭት ለመፍጠር፣ አካባቢው የሕዳሴ ግድብ መገኛ መሆኑን ተከትሎ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በዚህም እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር ትልቅ ጥፋት የመፍጠር ዓላማ ያለው ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ “በተለይም አሁን ሀገርን እየመራ ያለው ፓርቲም ሆነ ለውጡ እኛን አይወክለንም” በማለት ወጣቱንና ሕዝቡን ለአመጽ የሚቀሰቅሰው ቡድን

Source: Link to the Post

Leave a Reply