በጎንደር የጥምቀት በዓል ላይ ለታዳሚዎች የተዘጋጀ ርብራብ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/203943

(ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር የጥምቀት በዓልን ለመታደም ለመጡ እንግዶች የተዘጋጀ ርብራብ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሠላምና ሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ገለጸ።
Image may contain: one or more people, crowd, tree, outdoor and nature
አደጋው ለመቀመጫነት የተሠራው ርብራብ እንጨት ድንገት በመንሸራተቱ መድረሱን የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋ መኮንን ተናግረዋል።

በአደጋው ሳቢያም በርብራብ እንጨቱ ላይ ተቀምጠው የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም በአደጋው ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል።
በአደጋው ከተጎዱት መካከል የተወሰኑት ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ ቀሪዎቹ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ከታካሚዎቹ መካከል አምስቱ ከባድ ጉዳት ያጋጠማቸው ሲሆን፥ ቀላል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎችና ሁለት የፀጥታ ኃይሎች ይገኙበታል ብለዋል።
ለታዳሚዎች የተሰራው እንጨት ከአቅሙ በላይ ሰው መያዙ ለአደጋው መንስኤ ነው ማለታቸውን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከተፈጠረው አደጋ ውጭ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳልነበረና ታቦታቱ በሠላም ወደ አድባራቱ መግባታቸውን ጠቅሰዋል።
Image may contain: tree, sky, outdoor and nature

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.