በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያይቷል

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%89%A0%E1%8D%95%E1%88%AA%E1%88%9A%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%8A%E1%8C%89-%E1%88%B2%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%89%A1%E1%8A%93-%E1%88%B2%E1%8B%AB%E1%88%B8%E1%8A%95%E1%8D%8D-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE/

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 1 ተሸንፏል።

ከሜዳው ውጭ ከመቐለ 70 እንደርታ የተጫወተው ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ትናንት በሊጉ ስድስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ሊጉን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ9 ነጥብ ሲመራ ሃዋሳ ከተማ በ7 ይከተለዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.