በ2 ወር ከ3 ሳምንት ልዩነት ሁለት ልጆችን የወለደችው እናት

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%89%A02-%E1%8B%88%E1%88%AD-%E1%8A%A83-%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%8D%E1%8B%A9%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5-%E1%88%8D%E1%8C%86%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%8B%88/

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ29 ዓመቷ ካዛኪስታናዊት እናት በ2 ወር ከሁለት ሳምንት ልዩነት ልጆች መውለዷ ተሰምቷል።

ሁኔታዋ ያስገረማቸው ዶክተሮችም እንዲህ አይነት ነገር ከ50 ሚሊየን ሰዎች በአንድ ሰው ላይ ብቻ የሚከሰት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ሊሊያ ኮኖቫሎቫ የተባለችው እና ነች በሁለት ወር ከሶስት ሳምንንት ወይም 11 ሳምንታት ልዩነት መንታ ልጆቿን የተገላገለችው።

የህክምና ባለሙያዎቹ እንደተናገሩት ከሆነ ሊሊያ ኮኖቫሎቫ የህክምና ክትትል ለማድረግ ወደነሱ በተጓዘችበት ውቅት ችግሩ መኖሩን እንደለዩ አስታውቀዋል።

ሊሊያ ኮኖቫሎቫ የመጀመሪያዋ ሴት ልጇን የመወለጃ ጊዜዋ ከመድረሱ በፊት በ7ኛው ወሯ የተገላገለች ሲሆን፥ ከመወለጃ ጊዜ ቀድማ የተወለደችው ለጅም በወቅቱ 850 ግራን ነበር የምትመዝነው ተብሏል።

በዚህም ህጻኗ ሴት ልጅ በልዩ የሙቀት ክፍል አንድትቆይ ተደርጎ እንደነበረም ነው የተገለፀው።

ሊሊያ ኮኖቫሎቫ ከሁለት ወር ከሶስት ሳምንታት በኋላ ሁለተኛ ልጇን የተገላገለች ሲሆን፥ ሁለተኟው ልጇም ወንድ ልጅ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

ሁለተኛው ልጅ ጊዜውን ጠብቆ የተወለደ መሆኑን እና ሲወለድም 2 ነጥብ 9 ኪሎ ግራም እንዳለውም ነው ያስታወቁት።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.