በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ እንግሊዝ፣ ፖርቹጋልና ፈረንሳይ አሸንፈዋል

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%89%A02020-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%8D%E1%88%AE%E1%8D%93-%E1%8B%8B%E1%8A%95%E1%8C%AB-%E1%88%9B%E1%8C%A3%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%8A%E1%8B%9D%E1%8D%A3-%E1%8D%96%E1%88%AD/

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 6 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል።

በምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው እንግሊዝ እና ቼክ ሪፐብሊክ አሸንፈዋል።

በሜዳዋ ኮሶቮን ያስተናገደችው እንግሊዝ 5 ለ 3 በማሸነፍ የምድብ መሪነቷን አስጠብቃለች።

በመጀመሪያው አጋማሽ 5 ጎሎች ያስቆጠሩት እንግሊዞች በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በደካማ የተከላካይ ክፍል 3 ጎል አስተናግደዋል።

በሌላ ጨዋታ ሞንቴኔግሮ በሜዳዋ በቼክ ሪፐብሊክ 3 ለ 0 ተሸንፋለች።

በምድብ ሁለት በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ፖርቹጋል ከሜዳዋ ውጭ ሊቱየኒያን 5 ለ 1 ማሸነፍ ችላለች።

የቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ 4 ጎሎቹን ማስቆጠር ችሏል።

ወደ ሉክዘምበርግ ያቀናችው ሰርቢያ ደግሞ 3 ለ 1 አሸንፋ ተመልሳለች።

በምድብ 8 ጨዋታዎች ደግሞ አልባኒያ አይስላንድን አስተናግዳ 4 ለ 2 አሸንፋለች።

በሜዳዋ አንዶራን ያስተናገደችው ፈረንሳይ 3 ለ 0 ስታሸንፍ፥ ሞልዶቫ ደግሞ በምድቡ መሪ ቱርክ 4 ለ 0 ተሸንፋለች።

እንግሊዝ፣ ዩክሬን፣ ጀርመን፣ ሪፐብሊክ ኦፍ አየርላንድ፣ ክሮሺያ፣ ስፔን፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ቤልጂየም እና ጣሊያን ከምድብ 1 እስከ 10 የየምድባቸው መሪዎች ናቸው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.