በ8ኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት 8 ተሸላሚዎች በጎ ተብለዋል ።

በ8ኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት 8 ተሸላሚዎች በጎ ተብለዋል ።

( አደባባይ ሚዲያ ጷግሜ 1/2012 ፤ Sep.6/2020)ከተሸላሚዎቹ መካከል 5 ግለሰቦች እና 3ተቋማት ይገኙበታል። ክብርት ፕሬዝደንት ሣኅለወረቅ ዘውዴ የዘንድሮው የበጎ ሰው የሽልማት ሥነሥርዓት የክብር እንግዳ ነበሩ።የድርጅቱን መስራች ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ የካቶሊካዊት ቤተክርሰትያን ካርዲናል ብርሐነ ኢየሱስ ሱራፌል እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትም በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።የ8ኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎችም የሚከተሉት ናቸው፡- 1.አቶ ካሊድ ናስር ባለፉት አምስት ወራት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት መኖሪያ ግቢያቸውን በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩ፤2. አቶ ኪሮስ አስፋው ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ አንድ መቶ ጊዜ የሕዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ፤3.አቶቢኒያም ከበደ ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን መሥራች 4. ጋዜጠኛ መሀመድ አል አሩሲ፤ በአረብኛ ቋንቋ ለአለም አቀፍ ሚዲያ ስለህዳሴው ግድብ የሚከራከር5.ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህሩ እንዲሁም በውሃ ዲፕሎማሲው ዘርፍ ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል። 6. ኢትዮ ቴሌኮም በዓመቱ ውስጥ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በሰራቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የ2012 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 7.የሕክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችየኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ከፊት የተሰለፉ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የ2012 የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመድረኩ የጤና ባለሞያዎችንና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመወከልም ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡8.የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ሠራተኞች በሙሉ በዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የህዳሴ ግድቡ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ሠራተኞቹን ወክለው ሽልማቱን ተቀብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply