ቢቢሲ ከሶፍትዌር እንከን ጋር በተያያዘ በአሰራሩ ላይ ችግር እንደገጠመው አስታወቀ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%89%A2%E1%89%A2%E1%88%B2-%E1%8A%A8%E1%88%B6%E1%8D%8D%E1%89%B5%E1%8B%8C%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8A%A8%E1%8A%95-%E1%8C%8B%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8B%AB%E1%8B%AB%E1%8B%98-%E1%89%A0/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቢቢሲ ከሶፍትዌር እንከን ጋር በተያያዘ በአሰራሩ ላይ ችግር እንደገጠመው አስታውቋል።

ቢቢሲ ከሶፍትዌር እንከን ጋር በተያያዘ የቀጥታ ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ የተቀረጹ መረጃዎችን በማስተላለፍ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም በቢቢሲ ዋናው የዜና ማሰራጫ ፋንታ ከሌሎች የድርጅቱ ስቲዲዮዎች መረጃዎች እንዲተላለፉ መደረጉ ነው የተገለጸው።

ቢቢሲ ኒውስ ቻናል እና ቢቢሲ ወርልድ ቻናል የቀጥታ ስርጭት የተቋረጡ ሲሆን፥ መረጃዎች ከተቀረጹ በኋላ አየር ላይ እንደሚውሉ ነው በዘገባው የተገለጸው።

የተቋሙ ሰራተኞች ውስጥ ለውስጥ መረጃዎችን የሚለዋዎጡባቸው እና የሚገናኙባቸው አሰራሮች ላይም ችግሩ መታየቱ ታውቋል።

ይሁን እንጂ የቢቢሲ ዌብ ሳይት ላይ ችግሩ ያለመከሰቱ ነው የተገለጸው።

አሁን ላይ የችግሮች መንስኤዎች መለየታቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ፈጥኖ ለማስተካከል አየተሰራ ነው ተብሏል።

በድርጅቱ የዜና አዘጋጅ የሆኑት ማርክ ኢያስቶን በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንዳሰፈሩት የችግሩ መንስኤ በለንደን ሚልባንክ ስቲዲዮ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ቀደም ሲል ቢቢሲ በሮቦት የታገዘ የካሜራ አገልግሎትን ጨምሮ አዳዲስ ሶፍትዌሮቸን በማላመድ ሂደት ለቴክኒክ ችግር ተጋልጦ የነበረ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ፦ bbc.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.