“ባለቤቴ የወደመውን ሰብል ስትመለከት ራሷን ሳተችብኝ፣ ልጆቼን ምን ላበላቸው ነው ብላ ተጨነቀችብኝ” – BBC News አማርኛ

“ባለቤቴ የወደመውን ሰብል ስትመለከት ራሷን ሳተችብኝ፣ ልጆቼን ምን ላበላቸው ነው ብላ ተጨነቀችብኝ” – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/E726/production/_114947195__114940555_740ab5e4-1532-4733-b62a-6d88584fbd60.jpg

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣ መንጋው በክልሉ 4 ዞኖች፣ 18 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች መከሰቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው 87 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል የሚሉት አቶ ተስፋሁን፣ ከእነዚህም መካከል 30 ሺህ 500 ሄክታር የሚሆነው የሰብል ምርት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply