ባለፈው አንድ ሳምንት በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሞት ቁጥር ግን ቀንሷል-የዓለም የጤና ድርጅት

ባለፈው አንድ ሳምንት በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሞት ቁጥር ግን ቀንሷል-የዓለም የጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፈው አንድ ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንና የሞት ቁጥር ግን መቀነሱን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስታወቀ።
 
በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫረስ ሲያዙ የሟቾች ቁጥር ግን መቀነሱን ድርጅቱ ገልጿል።
 
ይህም ከሳምንት በፊት ከነበረው የቫይረሱ ስርጭት የ6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተገለጸው ።
 
ይህም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተያዥ የተመዘገበበት ነው ሲል የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
 
በሁሉም የዓለም ክፍሎች በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ ያሳየ ሲሆን÷ በአውሮፓ 11 በመቶ በአሜሪካ ደግሞ 10 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንን ድርጅቱ ገልጿል።
 
ድርጅቱ አያይዞም በዓለም አቀፍ ደረጃ የወረርሽኙ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም የሞት ቁጥር ግን ቀንሷል ነው ያለው።
 
በዚህም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10 በመቶ መቀነሱ ተገልጿል።
 
በወረርሽኙ በጣም ከተጎዱ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ያስመዘገበችው የሞት ቁጥር ከበፊት ሳምንት ጋር ሲነጻጸር 22 በመቶ እና በአፍሪካ ደግሞ 16 በመቶ መቀነሱ ተገልጿል።
 
ይሁን እንጂ አሜሪካ እስካሁን ከተመዘገበው አዳዲስ የቫይረሱ ስርጭት ግማሹን እና ከተመዘገበው የሞት መጠን ደግሞ 55 ከመቶውን እንደምትወስድ ተመላክቷል።
 
የሞት መጠን ከቀነሰባቸው ሀገራት መካከል ኮሎምቢያ ፣ ሜክሲኮ ፣ ኢኳዶር እና ቦሊቪያ ተጠቃሽ መሆናቸው ነው የተገለጸው
 
ምንጭ፡-አልጀዚራ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ባለፈው አንድ ሳምንት በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሞት ቁጥር ግን ቀንሷል-የዓለም የጤና ድርጅት appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply