ባልደራስ በደብረ ብርሀን ከተማ የተሳካ ስብሰባ በማካሄድ የሸዋ ቀጣና አደራጆችን በይፋ መሰየሙን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

ባልደራስ በደብረ ብርሀን ከተማ የተሳካ ስብሰባ በማካሄድ የሸዋ ቀጣና አደራጆችን በይፋ መሰየሙን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በደብረ ብርሀን ከተማ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህንፃ አዳራሽ ውስጥ የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን አስታውቋል። ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ላይም የደብረ ብርሀን ወጣቶች፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ነጋዴዎችና የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል። የባልደራስና የመኢአድ ቅንጅት ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝተው በተለይ በባልደራስ ራእይና አደረጃጀት እንዲሁም በባልደራስ መኢአድ ቅንጅት አላማዎች ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ባልደራስ በዛሬው ቀን ሸዋን የሚያደራጁ አምስት አመራሮችን በይፋ ሰይሟል። በሌላ በኩል የደብረ ብርሀንን ወጣቶችን ወክለው የመጡ አመራሮች በደብረ ብርሀን ወጣቶች ስም ባልደራስን የሸለሙት ሲሆን ሽልማቱ የቅንጅቱ መሪ የአቶ እስክንድር ነጋ ፎቶ ግራፍን ነው። የደብረ ብርሀን ወጣቶች ሽልማት ትልቅ መልእክት ያለው ሲሆን ወጣቱ ከባልደራስ ጎን መቆሙን ቅንጅቱን መደገፉን እንደሚያሳይም ተገልጧል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መሪዎችም በመድረክ ላይ ስለ ቅንጅቱ አላማዎች በማስረዳት የሸዋ ወጣት ከቅንጅቱ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል። ባልደራስ ከአዲስ አበባ ውጭ ሲያደራጅ የመጀመሪያው ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የማደራጀት ስራውን አጠናከሮ ይቀጥላል ሲል ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply