ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ለሚከፍተው የእግር ኳስ  አካዳሚ ስምምነት ተፈረመ

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%89%A3%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%99%E1%8A%92%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%88%E1%88%9A%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8C%8D/

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኑ አንጋፋ ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ለሚከፍተው የእግር ኳስ አካዳሚ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽ ከክለቡ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም የስምምነት ፊርማውን ተፈራርመዋል፡፡፡

ክለቡ ከ17 አመት በታች ታዳጊ የሆኑ ውጤታማ የእግር ኳስ ስፖርተኞችን ለማሰልጠን የሚያስችለውን የስፖርት አካዳሚ ነው በኢትዮጵያ የሚከፍተው፡፡

ይህንን በማስመልከት የባየር ሙኒክ እግር ኳስ ልዑክ ቡድን በተገኘበት ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃን በመያዝ  ያጠናቀቁ የአዲስ አበባ ታዳጊ እግር ኳስ ክለቦች በአዲስ አበባ ስታዲየም ፌስቲባላቸውን አካሄደዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የስፖርት አካዳሚው የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በየአመቱ እንደሚታደስ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.