“ቤተ ክርስቲያን ሆይ፥ ፀሐይሽ አትጠልቅም” ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ታኅሣሥ 5 በሚሌኒየም አዳራሽ ይካሔዳል፤ ጸሎተ ምሕላ – ስብከተ ወንጌል – ቃለ ተዋስኦ – ድጋፍ ማሰባሰብ

Source: https://haratewahido.wordpress.com/2019/12/13/%E1%89%A4%E1%89%B0-%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%88%86%E1%8B%AD-%E1%8D%A5-%E1%8D%80%E1%88%90%E1%8B%AD%E1%88%BD-%E1%8A%A0%E1%89%B5%E1%8C%A0%E1%88%8D%E1%89%85/
https://haratewahido.files.wordpress.com/2019/12/his-grace-abune-natnael-briefing.jpg
ጸሎተ ምሕላ ጸሎት ይደረጋል፤ ወቅታዊ ፈተናዋ ይተነተናል፤ ድጋፍ ይሰበሰባል፤ 30ሺሕ የመግቢያ ትኬቶች በስርጭት ላይ ናቸው!
Tsehaysh Atelkim0

~~~

His Grace Abune Natnael briefing

  • ካህናትንና መምህራንን በብዛት ለማሠልጠን እንዲሁም የኪራይ ገቢ ለማስገኘት፣ በነቀምት የሀገረ ስብከቱ የልማት ይዞታ ላይ ለመገንባት የታቀደው ባለ7 ወለል ኹለገብ ሕንፃ ዲዛይን በጉባኤው ላይ ቀርቦ ማብራሪያ ይሰጥበታል፤
  • በአፋን ኦሮሞ እና በግእዝ ሥልጠና የሚሰጥበት ማዕከሉ፣ በ3ቱ አህጉረ ስብከት ተተኪ አገልጋዮችን የሚያፈሩ የአብነት ት/ቤቶችን ለማጠናከርና ለማስፋፋት ከታቀደባቸው በርካታ ማዕከላት ተጠቃሹ ነው፤
  • ጸሎተ ምሕላ፣ ስብከተ ወንጌል፣ የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ  ፈተና የሚተነትኑ ቃለ ተዋስኦዎች፣ የጉባኤው መርሐ ግብሮች ሲኾኑ፣ በባለሞያዎችና ከአህጉረ ስብከቱ በተውጣጡ ምእመናን የሚቀርቡ ገለጻዎችም ተካተዋል፤
  • በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚመራውን የዚኽን ታላቅ ጉባኤ ዝግጅት የተሳካ ለማድረግ፥ የሰንበት ት/ቤቶች፣ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ማኅበራት እና በጎ አድራጊዎች እየተረባረቡ ናቸው፤
  • የአህጉረ ስብከቱን መንፈሳዊ ፣ ማኅበራዊና ልማታዊ አገልግሎት በአግባቡ ለማከናወን የሚያስችል ጠቃሚ ግብአት የሚገኝበት እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያናችንና ለአገራችን ሰላምና አንድነት፣ አምላክን በጸሎት የምንጠይቅበት ጉባኤ ይኾናል፤ ብለዋል ብፁዕነታቸው፤
  • ብር 50 ዋጋ ያላቸው 30ሺሕ የመግቢያ ትኬቶች በሽያጭ ላይ ናቸው፤ “ከችግሩ ስፋት አንጻር የሽያጩ ገቢ ውስን ነው፤” ያሉት አዘጋጆቹ፣ ምእመናንና በጎ አድራጊዎች የሚቻላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ተማፅነዋል
  • ከነገ በስቲያ እሑድ፣ ታኅሣሥ 5 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ ከቀኑ 7፡00 እስከ 12፡00 በሚሌኒየም አዳራሽ በሚከናወነው በዚኹ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ፣ ከቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ ብፁዓን አባቶች፣ የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት ሓላፊዎች ጋራ ከ25ሺሕ ያላነሱ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
  • በአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ጥቃት የካህናትና ምእመናን መፈናቀል፣ የአብያተ ክርስቲያን መዘጋትና መዘረፍ፣ የነባር አብያተ ክርስቲያን ይዞታዎች ወረራና የመንግሥት አካላት ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠት፣ ኢአማንያን ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ኹሉ ቤት እየገዙ ‘ጸሎት ቤት’ በማለት ምእመናንን ለማስኮብለል የሚያደርጉት ቅሠጣ፣ የኦሮሚያ አህጉረ ስብከት የተጋረጣባቸው ከፍተኛ ፈተና እንደኾነ ሪፖርቶች ያስረዳሉ፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.