ቤንሻንጉል ክልል በዳንጉር ወረዳ በተከሰተው ጥቃት የሰዎች ሕይወት አለፈ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/181622

የቤንሻንጉል ክልል ቃል አቀባይ አቶ መለሰ በየነ በዳንጉር ወረዳ ስለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋት
በትናንትናው እለት የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
ሁለቱ ሰዎች የአማራ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ 11 ሰአት ገደማ ምርት እየሰበሰቡ በነበረበት ወቅት በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፎ ተገኝተዋል።
ከዛ በሁዋላ አንድ የጉሙዝ ተወላጅ ከገበያ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት ጥቃት ደርሶበት ህይወቱ አልፏል። የጥቃቱ ምክንያት እስካሁን ግልፅ አይደለም፣ ግጭት ነበር የሚል መረጃም አልደረሰንም።
ሰዎቹ ህይወታቸው አልፎ ነው የተገኙት። አሁን ላይ የተፈጠረው የህይወት ማለፍ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.