ቤንጃሚን ኔታንያሁ በሶሪያ ሰላም ማስከበር ጉዳይ ዙሪያ ለመምከር ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%89%A4%E1%8A%95%E1%8C%83%E1%88%9A%E1%8A%95-%E1%8A%94%E1%89%B3%E1%8A%95%E1%8B%AB%E1%88%81-%E1%89%A0%E1%88%B6%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%89%A0/

አዲስ አበባ ፣መስከረም 27፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ከበቅርቡ በሶሪያ የሰላም ማስከበር ዙሪያ ለመወያየት ከፕሬዚዳንት ፑትን ጋር ሊገናኙ ነው፡፡

ኔታንያሁ ይህን የተናገሩት በሳምንታዊው የካቢኔ ስብሰባ ላይ ሲሆን ፥ የሚገናኙኑበትን ቀን ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ኔታኒያሁ በጉዳዩ ዙሪያ ፕሬዚዳንት ፑቲንን በስልክ ያነጋገሯቸው ሲሆን በቅርቡ ተገናኝተው ሀገራቱ በሶሪያ ሰላም ማስከበር ዙሪያ ሰለሚኖራቸዉ ሚና ለመወያት መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሩስያ ባለፈው ዕሁድ በሶሪያ የሚገኘውን የአየር መከላከያ ወደ S- 3000 ሚሳኤል ሲስተም ያሳደገች ሰሆን፥ ይህ የሆነውም በሶሪያ ሲንቀሳቀሰስ የነበረው ተዋጊ አውሮፕላን በእስራኤል ወታደሮች ተመቶ መውደቁን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ይሁሂን እንጂ ሩስያ የሰራቸውን አዲስ የአየር ሃይል መከላከያ ሲስተም በቀላሉ የማክሸፍ አቅሙም ብቃቱም አለን የሚሉት የእስራኤል ባለሥልጣናት፥ ዋና ጠላታቸው ኢራን በሶሪያ በኩል ገብታ ጥቃት እንዳትፈፅም አስፈላጊውን ዝግጅት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በቀጠናው በሁለቱ አገራት የተከሰተውን አለመግባባት ለመፍታትም የሁለቱ መሪዎች መገናኘት ጥሩ መፍትሄ እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡

ኢራን በሶሪ በኩል የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ለሂዝቦላህ ታጣቂዎች ታደርሳለች በሚል ስጋት እስራኤል በቀጠናው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ምንጭ፦ሲጅቲኤን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.