ብሄራዊ የስራ ቋንቋን ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ጋር በዝቅተኛ የክፍል ደረጃ መሰጠት እንዲጀመር የተቀመጠው ሃሳብ አከራከረ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/142556

በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ተጠናቀቀ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል።
ጉባኤው በቆይታው የ2011 አም የእቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ ላይ የመከረ ሲሆን፥ በሶስተኛው ቀን ውሎም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ መክሯል።

በዚሁ ፍኖተ ካርታ ላይም በአመዛኙ አተገባበሩ ላይ ቢስተካከሉ እና እንደገና ቢታዩ ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል ጉባኤተኛቹ።
በዚህም ፍኖተ ካርታውን ለመተግበር የሽግግር ጊዜና ከቀደመው ስርአት መውጫ ስትራቴጅ ያስፈልጋል፣ለመምህራን የተሰጠው ስልጠና በቂ አይደለም፣ የመፅሀፍ እና ትምህርት ግብአት ዝግጅት በበቂ ሁኔታ አልተሟላም፣ ሁሉም ሳይስማማበት ወደ ትግበራ መግባቱ ችግር ይፈጥራል፣ ያልተወያዩ ክልሎችና የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ፣ የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።
በተጨማሪም ጉባኤተኛው በፍኖተ ካርታው የክልልና የፌዴራል ሃላፊነት በግልፅ አልተቀመጠም፣በምን መልኩ እንደሚተገበር ግልፅ አልሆነም፣ መምህራን በተመለከተ የተቀመጠው በስራ ላይ ያሉትን ያላገናዘበ ነው፣ ለአርብቶ አደሮች ልዩ ስትራቴጅ ይዘጋጅላቸዋል የሚለው በግልፅ አልተቀመጠም፣ የሚሉ ነጥቦችንም አንሰረተዋል።
ከዚህ ባለፈም የ8ተኛ ክፍል ፍኖተካርታው ሲተገበር የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች እጣ ፋንታ ምን ይሆናል፣ የ8ተኛ ብሄራዊ ፈተናን የሚያዘጋጀው ማን ነው የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል በተሳታፊዎቹ።
ብሄራዊ የስራ ቋንቋን ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ጋር በዝቅተኛ የክፍል ደረጃ መሰጠት እንዲጀመር የተቀመጠው ሃሳብም በስፋት አከራክሯል።
በአንዴ ከመጫን ይልቅ ደረጃ በደረጃ ቢተገበር፣ ፍኖተ ካርታውን በተመለከተ በሁሉም ዘንድ ተመሳሳይ አቋም ቢያዝ፣ ከመተግበሩ በፊትም የፓሊሲ መከለስ ስራው ቢቀድም፣ በህግ መታየት ያለባቸውም በቶሎ ምላሽ ያግኙ የሚሉት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.