ብሄራዊ የአንድነት ቀንና የአዲስ አመት ዋዜማ በብሄራዊ ቤተ መንግስት እየተከበረ ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/145766

ብሄራዊ የአንድነት ቀን እና የአዲስ አመት ዋዜማ እየተከበረ ነው
(ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ የአንድነት ቀን እና የአዲስ አመት ዋዜማ እየተከበረ ነው።
ቀኑ በተለይም በብሄራዊ ቤተ መንግስት እየተከበረ ይገኛል።
Image may contain: 5 people, people standing and text

በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
መድረኩንም የሃይማኖት መሪዎቹ በምርቃት ያስጀመሩት ሲሆን፥ መጭው አዲስ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የብልጽግና ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ጳጉሜን በመደመር እሳቤ ከጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ እየተከበረ ሲሆን በዛሬው እለትም ፍጻሜውን ያገኛል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.