ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ተባለ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%91-%E1%89%B0%E1%8A%AD%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%88%AC%E1%8B%B5%E1%8A%93-%E1%88%98%E1%8A%AE%E1%8A%95%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%8C%88%E1%88%B0-%E1%8D%8D%E1%88%AD%E1%8B%B5/

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) አዲስ አበባ ላይ ትላንት በቁጥጥር ስር የዋሉት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ታወቀ።

ፍርድቤት ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ እንደነበርም መረጃዎች አመልክተዋል።

በአዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አስተባባሪዎች አንዱ የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ በ9 የፌደራል ፖሊስ አባላትና በሶስት ደህንነቶች ትላንት በቁጥጥር ስር የዋለው አንድ ሆቴል ውስጥ መሆኑም ተመልክቷል።

 

The post ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ተባለ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.