ብጄኔራል አሰምነው ጽጌ! የዘመናችን ታናሹ በላይ ዘለቀ!!!

Source: https://welkait.com/?p=19565

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio semay) ቅዳሜ ከከተማየ ወጣ ብየ ነበር። አንድ ወዳጄ ደውሎ አዲስ ዜና አለ አለኝ። ስንጓዝበት የነበረው ድልድይ ረዥም እና ስልክ ለማስተላለፍ ስለማያመች “በደምብ ማድመጥ ስላልቻልኩ ዘጋሁት”። ትኩስ የተባለውን ዜና ለማድመጥ ቸኩዬ ሲመሻሽ እቤት ስገባ ላንድ የቅርብ ወዳጄ ስልክ ደውየ፤ ምን ተፈጠረ? አልኩት። የሆነውን ሁሉ ነገረኝ። በስፋት ለማወቅ ድረገጾች ላይ ስፈትሽ ወዳጄ …

Share this post

One thought on “ብጄኔራል አሰምነው ጽጌ! የዘመናችን ታናሹ በላይ ዘለቀ!!!

 1. የግድያው ድራማ ታውቋል
  1. ደራማው በብዙ በጥቂቱ እንዲህ ነው፡፡ ብአዲን ስብሰባ አድርጎ ጀንራል አሳምነውን ለማውረድ አብይ ለአምባቸው ትእዛዛዝ ሰጥቷል።
  2. ተሰብሳቢዎቹ የብአዴን አባላት ባይስማሙና ጀነራል አሳምነው በሀሳቡ ባይስማማ በሀይል ለማፈን አብይ እቅድ አውጥቷል።
  3. አብይ በጉብኝት ሰበብ ባሕር ዳር የራሱን ጠባቂዎችና የተወሰኑ የፌደራል ወታደሮች ይዞ ከግድያው በፊት ባሕርዳር ገባ። ምክንያቱም የአማራ ክልል የፀጥ አስከባራዎች ጀነራል አሳምነውን ለማፈን ስለማይችሉ።
  4. የአብይ የፈዴራል ወታደሮች ጀነራል አሳምነውን ለማፈን ሲሞክሩ ግጭት ተነሳ።
  5. የጀነራል አሳምነው ጠባቂዋች ጀነራል አሳምነውን ከቦታው ያሸሻሉ።
  6. በተነሳው የቶክስ ልውውጥ የዶክተር አብይ አጃቢዎች እና የፊደራል ወታደሮች እነ ዶር አምባቸውን ይገላሉ።
  7. ዶክተር አብይ ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት እንዲገባላቸው ብ. ጀነራል ሳእረን ይጠይቃሉ፡፡ ሲራው ያልገባቸው ሳሕረም ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ለአብይ ይነግሩታል።
  8. አብይ ጀንራል ሳእረን በጠባቂያቸው አስገድሎ፤ በምክትሉ ትእዛዝ ወታደር ወደ ባሕር ዳር እንዲገባ ያደርጋሉ።
  9. አብይ ያመጣቸው ጠባቂዎቹ እና የፌድራል ወታድሮች በባሕር ዳር ጀነራል አሳምነውን በመያዝ፤ ጉዳዩን መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አደረጉት
  የአብይ አህመድ በባህርዳር የሰራው ድራማ በዚህ መልኩ ተፈጸመ!! by Endale Asmare
  *******************************::
  ዶ/ር አብይ አህመድ በታህሳስ 2009 ዓም አካባቢ አንዲት ወደ 173 ገጽ የምትሆን “እርካብና መንበር” የሚል የመጽሃፍ ርዕስ ያላት መጽሃፍ ጽፎ ነበር፡፡ ዶር አብይ በጻፈው መጽሃፉ በገጽ 38 ላይ እንዲህ ይላል፡-
  “ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደ ምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው። ከዚያም “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ይህን መሰሉ ለዘብተኛ የኃይል አጠቃቀም ዘዴ ሰላም ሳይበጠበጥ ህዝብም ሳያጉረመርም የተደላደለ ስልጣን ባለቤት ለመሆን ያግዛል።”
  ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
  መፈንቅለ ክልል ? መፈንቅለ ፕሬዘዳንት ? መፈንቅለ ክልላዊ መስተዳድር ? ይህ በራሱ የተፈናቀለ ወሬ ነው:: ከመቶ አሥር ሚሊየን ሕዝብ ሶስት አማራና ሁለት ትግራዋይ የተሰውበት ፍንቀላ!??
  ** ጠ/ሚ ኮሎኔል ዓብይ አህመድ ለጎረቤት የአፍሪካ ሀገሮች ለክልል መፈንቅለ መንግስት “እንምጣና እንርዳህ?” ላሏቸው በአማርኛ እየተናገሩ “የውስጥ ጉዳያችንን እኛው እንጨርሰዋለን ስንፈልጋችሁ እናሳወቃችኋለን” ብለው ወዳጆቻቸውን አጽናኑ?! ሰሜን ተራራ ደን በእሳት ሲጋይ ያልመጡ ዛሬ እንዴት ጆሮአቸው ቆመ? ባለፈው ዓብይ ሊፈናቀል ሲል የሰበታ ለገጣፎ፡ ሱሉልታና ሰንዳፋ ፈረሰኞች መንግስታችን ተነካ ብለው አራዳ ደርሰው ነበር አይደል? ዓብይ(አብዮት) ይቺ የሚሊሻ: የአብዮት ጥበቃ ጥብቆ የት ያሰፋት ትሆን!?
  “ሟችም ገዳይም ወገኖቻችን” ናቸው ሲል ኦቦ ለማ መገርሳ ጉዳዩ የራሳቸው የቤት ውስጥ ነው ሲል ጀግንነት ለአማራው: ማን ለሕዝቡ የቆመ እንደሆነ ማን ሕዝቡ ላይ እንደቆመ መመስከሩ ነው::
  ** ዶ/ር ደፂ ግን ክልላዊ የማጥራት ዘመቻ(የግድያው)ራዕይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ቡኣ! ያለው ጧ! ያለው ይሆናል ማለቱ ነው?
  ** ሐዘን የገባቸው አጽናኝዎች የአማራ ክልል ሕዝቦችና የኢትዮጵያ ሕዝቦች እግዝሐብሔር ያጥናችሁ ይላሉ! የአማራ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ወጭ ሆኖ መፈንቀለ መንግስት ደረሰበት ? ድንቄም! ባለፈው ግዜ “ሕገመንግስቱንና ሕገ መንግስት ሥርዓቱን በኅይል ለመናድ አንድ ክላሽና ሶስት ሺህ ብር እጅ ከፍንጅ ተያዘ” ይባል ነበር:: ዛሬ ደግሞ ጡረተኛ ሜ/ጄ ገዛይ አበራን ገሎ መፈንቅለ መንግስት የሚያደርግ ጄ/ል አሳምነው ፅጌ ? ወይም(ሃያ ሰባት ዓመት) ሲያወናብድ የነበረውን ሳሞራ የኑስ ሳይገል ድምጹ ያልተሰማ በአንድ ዓመቱ ጠ/ኤታማዦር ሰዓረ መኮንን ለመግደል እንዴት ተወሰነ? ገዛይ አበራ ሰዓረ መኮንን ገደለው ለማለት የተነደፈው ተውኔት እንዴት አልተሳካም? እነ ተፈራ ዋልዋ ከሳተላይት ተከላ ችግኝ ተከላ ሲሳተፉ እንዴት ፍንቀላ ሆነ?
  ** የሆነ ሆኖ የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጠባቂ በጥበቃ ጓዶቹ ቆስሎ ተይዞ እንዴት በሶስተኛው ቀን እራሱን ወዲያው እንዳጠፋ አጥፍቶ ጠፊ ሆነ?
  **የክልሏን መፈንቅለ ቱልቱላ ትታችሁ: ባለፈው ኅላፊው ማን እንደሆነ ያልታወቀው የኢንተርኔት ማጥፋት ሳምንት ጀምሮ የነበረውን ፌደራላዊ ፍንቀላ እምቢልታ ሚስጥር ለሕዝብ ንገሩ! ፈተና አውጥታችሁ የሸጣችሁበትን ክልል ኢንተርኔት ከፍታችሁ: ተማሪ እንዲወድቅ የዘጋችሁበትን ክልል ዓለም አውቆታል ጸሐይ ሞቆታል!! ይሰማል?
  ” አማራ ክልል መደራጀት አለበት: ተከቧል! እስከዛሬ በየዋህነት የደረሰበት በደል ይበቃል!: ሙህራን: የሃይማኖት አባቶች: ካድሬዎች አርፋችሁ ተቀመጡ! በውሸት የዕርቅ ስብከት ትውልዱን አዘናግታችሁ አማራን ታስፈጃላችሁ” ሲል የተደመጠው ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ትክክል አደለም! አያገባህም! ከተባለ ውሳኔው ትክክል ነው:: አማራ መሳይና አማሳይ አሁን ቢያላዝን: ወደፊትም ጀሌው ተበደለኩ: ተፈናቀልኩ: ተወረርኩ:ተገረፍኩ ተኮላሸሁ ቢል ጀግናውን በልቷልና አፉን ዝንብ ይወረዋል እንጂ ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የነበረው ወረራ: ታሪክ ሃይማኖትና ዘር የማጥፋቱ ሁኔታ:በረቀቀ ዘዴ በልዩ ጥቅማጥቅም ሰጥቶ መውሰድ መርህ ጀምሯል፡፡ አዳሜ የሚጠቅመውንና የሚጠቀምበትን ሳያወቅ እንዲሁ በእየሜዳው ጥይት እያንኳኳ በባዶ እግሩ: በባዶ ሆዱ: ቂጡን ገልቦ ያናፋል? ማፈሪያ……በለው!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.