ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሰላም መደፍረስ እንዲከሰት ሲያሴሩ በነበሩ ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ታወቀ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/176221

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጥፋት ፈጸሙ ባላቸው ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚታየውን ወቅታዊው የሰላም መደፍረስ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲከሰት ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለሁ ያላቸውን ተማሪዎች የከፋ ጥፋት ሳይደርስ ቀድሞ በመለየት እርምጃ መውሰዱን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በተመሳሳይ ድርጊት የተጠረጠሩትን ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች ለይቶ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ ገልጸዋል፡፡
ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር በተወሰደው እርምጃ በዩኒቨርሲቲው አሁን ያለው ሁኔታ ፍጹም ሠላም መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አክለው መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.