ቦይንግ የአሜሪካን አብራሪዎች በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያላቸውን ሥጋት ሰምቶ ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ መከላከል ይቻል ነበር ተባለ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/119095

ቦይንግ የአሜሪካን አብራሪዎች በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያላቸውን ሥጋት ሰምቶ ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ የደረሰውን አደጋ መከላከል ይቻል ነበር ተባለ።
የአሜሪካ አውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር ቃል አቀባይ ዴኒስ ታጀር ቦይንግ የአብራሪዎቹን ጥቆማ ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገጠመውን አደጋ መከላከል የሚቻልበት ዕድል ይኖር ነበር ሲሉ ለሲኤንኤን ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ ኩባንያው የፈጸመው ተግባር አሳፋሪ መሆኑን ጠቅሰው ወቅሰውታል።

ቦይንግ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ኃላፊነቱን ለመውሰድ እንዳፈገፈገ ይገኛል። ባለሙያዎች ግን የ737 ማክስ አውሮፕላኖች መሰረታዊ የንድፍ ስህተት አለባቸው ሲሉ ይሞግቱታል። ቦይንግ 737 ማክስ የኤየር ባስን ኤ–302 የአውሮፕላን ሞዴል በዓለም ገበያ ለመወዳደር የተሰራ ነው። ቦይንግ እና ኤየር ባስ በአውሮፕላን ገበያ የጦፈ ውድድር ውስጥ ናቸው። አንዳቸው የተሻለ የአውሮፕላን ሞዴል ከሰሩ ሌላው ከፍተኛ ገንዘብ ያጣል። የሆነውም ይኸው ነበር። ኤየር ባስ በ2010 ዓ.ም. A320 የተባለውን ሞዴል አሻሻለ። ይኸ ሞዴል የነዳጅ ፍጆታው በ15 በመቶ ገደማ የቀነሰ ነበር። የተሻሻለውን ሞዴል ኤ320 ኒዎ(A320neo) ሲሉ ጠሩት።
የቦይንግም ሆነ የኤይርባስ አዳዲስ አውሮፕላኖች በበረራ ወቅት የነበራቸውን ፍጆታ ቢቀንስም የሞተሮቻቸው ግዝፈት ጨምሯል። ይኸው የሞተር ጉዳይ ቦይንግ ን ጣጣ ውስጥ ከቶታል።
Via Eshet Bekele
Photo: Elias Meseret

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.