ቮይዝ ኩባንያ ለግልገል ጊቤ 2 የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የአማካሪነት ስምምነት ፈረመ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%89%AE%E1%8B%AD%E1%8B%9D-%E1%8A%A9%E1%89%A3%E1%8A%95%E1%8B%AB-%E1%88%88%E1%8C%8D%E1%88%8D%E1%8C%88%E1%88%8D-%E1%8C%8A%E1%89%A4-2-%E1%8B%A8%E1%8A%A4%E1%88%8C%E1%8A%AD%E1%89%B5%E1%88%AA%E1%8A%AD/

አዲስ አበበ፣ ህዳር 11፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ቮይዝ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ለግልገል ጊቤ ቁጥር 2 የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአማካሪነት ለመስራት ስምምነት ፈርሟል።

ስምምነቱ በትናንትናው ዕለት በጀርመን በርሊን በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ኢንቨስትመንት ጉባኤ ጎን ለጎን የተፈረመ ነው።

ስምምነቱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የቮይዝ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ክለሴን ተፈራርመውታል።

የኮንትራት አገልግሎት ስምምነቱ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፥ ይህም ፕሮጀክቱ የሚያመነጨውን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅም ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

በስምምነቱ መሰረት ኩባንያን ዘመናዊ እና ዲጂታል የሆኑ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጥገና አሰራሮች እና አገልግሎቶችን የሚዘረጋ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም በዘርፉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር የሚያካሂድ መሆኑ ተገልጿል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.