ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል ላለመላክ ስለያዘው አቋም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከትግራይ ክልል ጋር ለውይይት ተቀመጠ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/158714

Reporter amharic

የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል ላለመላክ ስለያዘው አቋም፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየተነጋገረ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የውይይቱ ውጤትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ክልሉ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ መሆኑን በመጥቀስ ነው፣ ወደ አማራ ክልል ተማሪዎችን እንደማይልክ ያስታወቀው፡፡ በዚህ ዓመት 9,000 የትግራይ ተወላጆች ወደ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል የሚያስችላቸውን ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን፣ ከእነዚህ ውስጥ አማራ ክልል ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ የተመደቡት 2,000 እንደነበሩ፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመወያየት ቁጥራቸው ወደ 600 ዝቅ እንዲል መደረጉን የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገብረ መስቀል ካህሳይ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር 40 በመቶ አዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በክልላቸው እንደሚመደቡ፣ 60 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ተለያዩ ክልሎች ይላኩ እንደነበር ገልጸው፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በበዙበት በዚህ ወቅት ግን ይህ ተቀይሮ በክልላቸው የሚመደቡ ተማሪዎች መጠን ወደ አሥር በመቶ ዝቅ ማለቱን ወደ ሌሎች ክልሎች የሚደለደሉት ደግሞ ወደ 90 በመቶ ከፍ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ብለዋል ኃላፊው፡፡
በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ የተመደቡት 600 ተማሪዎች ሌላ ቦታ እንዲመደቡ እንደሚሠራ፣ ይህ ካልሆነ ግን የትግራይ ክልል ሌላ አማራጭ ይፈልጋል የሚል አቋም መያዙን ገብረ መስቀል (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
‹‹በመርህ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች ተጠሪነታቸው ለፌዴራል መንግሥት ነው፡፡ የክልል መንግሥታት መቆጣጠር የሚችሉት በቋንቋቸው የሚሠሩባቸውን የመምህራን ማሠልጠኛና የግብርና ኮሌጆችን ነው፤›› ያሉት የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.