ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን? | በፍቃዱ ዘ-ኃይሉ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=82599

ከዓመታት በፊት አንድነት ፓርቲ በሕይወት ሳለ፣ የቀድሞዎቹ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት አቶ ስዬ ኣብርሓ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲውን ሊቀላቀሉ ሲሉ ትልቅ ፌሽታ ሆኖ ነበር። እንዲያውም ‘መርሕ ይከበር’ በሚል የተገነጠለው ቡድን፣ እነርሱን ለመቀበል የተዘጋጀውን ድግስ በአመፅ እስከማደናቀፍ ደርሷል(?)። ቅራኔው “እነርሱ የተለየ አቀባበል የሚደረግላቸው የገዢው ፓርቲ የቀድሞ አባል ስለሆኑ ነወይ?” የሚል ነበር። ተቃዋሚው የቀድሞ የኢሕአዴግ አባል ለቅቆ ሲወጣ […]

Share this post

One thought on “ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን? | በፍቃዱ ዘ-ኃይሉ

 1. ህወሀት በሞተር ዘይት ቅየራ ላይ!
  (ምስጋናው አንዱዓለም)
  የአንድነት መዝሙሩን ካልተጠበቀ አቅጣጫ ማሰማት። ለዚህ ያው እንግዲህ ሁሉም እንደሚያውቀው ከኦህዴድ አካባቢ እንዲዘመር ማድረግ ነበር፤ እየሆነ ያለውም ያው ነው። በዚህም ብአዴንን አጋር አድርጎ የይምሰል አንድነት መገንባት። እየሆነ ያለው ማለት ነው። አሁን በብአዴን እና በኦህዴድ መካከል እየተደረገ ያለውን እውነተኛ ሂደት ለመረዳት አስቸጋሪ የሚመስሉ ነገሮች አሉ። ምናልባት በምእራባዊያን ዘንድ ታማኝ ወኪል የሆነው ህወሀት ከአዛዦቹ ጥገናዊ ለውጥ እንዲያደርግ ተመክሮ ይሆናል። ይሄም ከራሱ ከህወሀት የረዥም ጊዜ እቅድ ጋር በተሳሰረ መልኩ የሚፈጸም ስለሆነ አስቸጋሪ አይደለም። በዛም አለ በዚህ ህወሀት ምን አልባት ኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር ለማስቀመጥ አስቦ ሊሆን ይችላል። ያ ቀጣይ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር ደግሞ በአማራ ህዝብና (በህወሀቱ ስሪት ብአዴን) ተአማኒነት እንዲያገኝ ያስፈልጋል። ለዛ ደግሞ ብቸኛው መንገድ የአንድነት መዝሙር ቀድሞ መዘመር ነው። ካሁኑ እንዲህ አይነት ዝግጅት ከተደረገ ደግሞ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር በሚሾምበት ጊዜ በአማራም በኦሮሞም ያለው ህዝባዊ ግለት ይበርዳል ተብሎ ታስቦ ይሆናል።

  አንድ ነገር መሰመር ያለበት ግን የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር ቢመጣም ከሀይለማርያም የተለየ ሚና እንደማይኖረው ነው። ምክንያቱም እንደ ደኢህዴን ሁሉ ኦህዴድ በመላው ኢትዮጵያም ሆነ በአለም ዙሪያ አይደለም ከህወሀት የሚወዳደር ጫማው ስር የሚጠጋ የደህንነት መዋቅር የለውም፤ ይሄንን የህወሀትን መረብ አልፎ ሊዘረጋም አይችልም። ህወሀት የደህንነት እና የጦር ሰራዊት መሰረተ ልማቶችን ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠርበት ሁኔታ ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታ ለኦህዴድ ቢሰጥ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም። በአንጻሩ የኦሮሞን ተቃውሞ ዝም ለማሰኘት እና የአማራውን ወገን ለማዘናጋት ይጠቅማል። ያ ደግሞ ለህወሀት ከሞተር ዘይት ለውጥ በኋላ ተጨማሪ እድሜን እና ራሱን ለማስተካከል ታካይ እድልን ከመፍጠር የዘለለ ሚና የለውመ። ስለሆነም አሁንም ዋናው ተዋናይ ህወሀት ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው። እንዲያውም ህወሀት የኦህዴድን ሰው ጠቅላይ ሚንስትር በማድረግ ከቻለ ትልቅ የፖለቲካ ስኬት ነው።

  በመጨረሻም መዘንጋት የሌለበት ሀቅ ሸክላ ሰሪ በሸክላው ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው መሆኑ ነው። እንዴት እንደሰራኸው የምታውቀውን ሸክላ እንዴት እንደምታሰራውና እንዴት እንደምትሰብረው ሙሉ እውቀቱ አለህ። የኦህዴድም ሆነ የብአዴን ባለስልጣናት አይደለም ፖለቲካዊ አካሄዳቸው እስትንፋሳቸው ራሱ በህወሀት የደህንነት አካል መዳፍ ስር ነው። (ለቀልድ ያህል፡- ለመሆኑ ለማ መገርሳን ይዞ ባህር ዳር የሄደው አውሮፕላን አብራሪ ኦህዴድ ይሆን?) በተጨማሪም ገዱ አንዳርጋቸው እና የተቀሩት ክበቦቹ ለአማራ ህዝብ ጥቅም ሊቆሙ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። ቢፈልጉ እንኳ አይችሉም። ግጨውን ተደብቆ በአሳቻ ሰአት ፈርሞ የሰጠ ብአዴን መቸም ያለ ህወሀት ፈቃድ ከኦህዴድ ጋር አስረሽ ምችው ሊደነክር እንደማይችል መገመት ከባድ አይደለም።

  እናም አሁን እየሆነ ያለው በህወሀት ቀማሪነት የሚካሄድ የህወሀት “ግራንድ ዲዛይን” ነው፤ እየሆነ ካለው ሁሉ አንዳች ስንኳ ከህወሀት እቅድና ፈቃድ ውጭ የሆነ ነገር የለም ለማለት ያስደፍራል። ይህ የግል አስተያየት ትክክል ነው ተብሎ ይታሰባል። ነገር ግን ስህተት ያለባቸው አረፍተ ነገሮችን ያካተተ የማይሆንበት እድልም የለም። በዛም አለ በዚህ ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል። ለአሁኑ ግን ህወሀት የሞተር ዘይት እየቀየረ ነው ብሎ መደምደም የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነን። ምናልባት ጥልቅ ተሀድሶ የተባለው እውነተኛ ባህርይም አሁን እየተካሄ ያለው ሊሆን ይችላል……
  **************!
  (መጪው ዘመን የኦሕዴድና ብአዴን የከፍታ ዝላይ!)
  ኦሕዴድ እና ብአዴን እውን ሕወሓት ላይ አምፀዋል? ህወሓት የሻቢያን ጥርስ አውልቆ ኮንፌደሪሽን መሥርቶ አዲስ ካርታ ቢዘረጋስ? አብዮት ልጇን ትበላለች። የኢሕአዴግ አባሎች እንቢታ ምን ፋይዳ አለው? አካባቢን ለማስተዳደር በአቅም ማነስ፡ ሠላምና ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነትን ተቀብሎ የዜጎችን ደህነነት ባለመጠበቅ፡ ለድህነት ቅንሳ እንቅፋት፡ ለልማት ደንቃራ ብሎ ቀድሞ ግንባር የሚባል ይቅርና ውሕደት ብሎ ቢበተናቸውስ!? ኦህዴድ ኦሮሞ ነው ብአዴን ማነው!?
  “ኦሕዴዶች ጉባኤያቸው ላይ ባሳለፉት አቋም፣ በሚሰጧቸው መግለጫዎች ለኢትዮጵያዊ ኅብረት ያላቸው ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ መግባት እንደሌለበት በመሐላ እያረጋገጡ ነው። ፯ኛ መደበኛ ጉባዔያቸው ላይ አቋም ከወሰዱባቸው ነጥቦች አንዱ “የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም እና የኢትዮጵያውያንን ኅብረት ጉዳይ የማይደራደሩበት” መሆኑን ገልጸዋል። የጥቅምት ፳፭-፳፯ቱ የምክክር መድረክ ዓላማም ይኸው ይመስለኛል።”

  ሕወሓት ለምን ዝም አለ?
  — ብአዴን ሲተብት፣ ኦሕዴድ ሲያፈነግጥ – አለቃ ተብዬው ሕወሓት ለምን ዝም አለ? እስኪ ማን ማን እንደሚያፈነግጥ ልያቸው እና ለቃቅሜ ልክ አስገባቸዋለሁ ብሎ ነው? ወይስ፣ የራሱ ሴራ ስለሆነ (በዚህ አጋጣሚ ተቃውሞው ስለታገሰለት፤ እንዲሁም ዳያስፖራው ከጫወታ ውጪ ስለሆነ) ደስ ብሎት ነው?
  * ብአዴን+ ኦሕዴድ+ ዲያስፐር+ ልሂቃን+ አክቴዎች =(ተልባ)
  __ ለመሆኑ ሕወሓት ከዛሬ ጀምሮ በሕዝብ ፍላጎትና ጥልቅ ተሃድሶ፡ ለኢትዮጵያ ከፍታ ሲባል አረንጓዴ፤ ቢጫ፤ ቀይ፤ ሰንደቅ ዓላማን (ልሙጡን) ማንቸውም ዜጋ ቢጠቀም ወንጀል አይሆንም ቢል ፮ ዝንጉርጉር ሰንደቅ ያላቸው ክልላዊ ሠፈሮች እንኳን ሊገጥሙ፡ ሊያምጹ፡ ሊተብቱ አብራችሁ ትቆማላችሁን?። ለኦነግ/ኦፌኮ/ዲያስፐር/ኦህዴድ ‘በልዩ ጥቅማጥቅም’፳፮ ዓመት በነጻ መሬት ከጋለበ፡ ልዩ ጥቅማጥቅሙን ገፎ ማቆራረጥ ወይም ለብአዴን ተቃራኒ ጥቅማጥቅም ሰጥቶ ማናቆር(የተካኑበትን) ለዚህ ፍቃደኛ ያልሆናችሁ እርስ በእርስህ ከግንባር ፓርቲ ግንባራችሁን ተበጣርቃችሁ ትለያያላችሁ። በእርግጠኝነት ህወሓት የሚያስማማችሁን ሲኮተኩት የሚያለያያችሁን እንደሚያጸድቅባችሁ ማሰብ ነው!። ታሪክ ያወረሰንን የተዛባ ግንኙነት በጠስን ቢልስ? አንድ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ግንባታ(ትሪሊየን)ኪሳራ ሆኗል በአንድ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ሥር ተጠቃለሉ ቢልስ? ቱ ቱ

  Reply

Post Comment