ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት ላይ እምነት አጥተናል አሉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/153494

በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት ላይ እምነት አጥተናል
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከወራት በፊት ለመወያየት ቅደም ተከተል ባስቀመጡት የመወያያ አጀንዳ እንዲወያዩ ዛሬ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጥሪ አቅርቦላቸው ነበር” ከውጭ በመጡት፣ ሀገር ውስጥ ባሉትና በምዝገባ ሂደት ላይ ባሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ ላይ ለውይይት ቢቀመጡም ፤ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነቱ ላይ እምነት አጥተንበታል፣ ህልውናችንን የሚያከስም የምርጫ ህግ ሲጸድቅ ዝም ብሎ ተመልክቷል፤ ስለሆነም መወያየት ያለብን በዚህ ጉዳይ ነው፤በማለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምረው እስከ 6 ሰዓት ድረስ ጉንጭ አልፋና አወያዮች ከያዙት አጀንዳ ውጭ በሆነ ሃሳብ ላይ ሲነጋገሩ ውለዋል።

በመጨረሻም በቀጣይ በሚደረግ ዉይይት በሌላ ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ባሉት ጉዳይ ላይ ለመወያየት ተስማምተው የዛሬውን ውይይት በዚህ ሁኔታ ቋጭተውታል። ፖርቲዎቹ በቅርቡ የጸደቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ያለ አግባብ የጸደቀ በመሆኑ መንግስትም ሆነ ምርጫ ቦርድ ከወዲሁ ዳግም እንዲያዩትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አሳስበዋል። እንድንወያይበት ቅደም ተከተል የሰጠነውን አጀንዳ ማምጣታችሁ ተገቢ ቢሆንም ወቅታዊ የሆነ ጉዳይ ባለመሆኑና ይህንን ስምምነት ከፈጸምን በኋላ እየተከሰቱ ያሉት ጉዳዮች አሳሳቢ በመሆናቸው ቅድመፐያ አዋጁ ላይ እንድንወያይ በሚል አወያዮች ላይ ከፍተኛ ትችት ሰንዝረዋል። ይህንን ተከትሎም በየትኛው አጀንዳ መቼ እንደሚወያዩ ባይወስኑም የዛሬውን ውይይት በቀጠሮ በትነውታል።
ቪዲዮ፤ DW_ሰለሞን ሙጬ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.