ተጠርጣሪውን በእባብ ያስፈራራው መርማሪ ፖሊስ ይቅርጣ ጠየቀ

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%88%AD%E1%8C%A3%E1%88%AA%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8A%A5%E1%89%A3%E1%89%A5-%E1%8B%AB%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%88%AB%E1%88%AB%E1%8B%8D-%E1%88%98%E1%88%AD%E1%88%9B%E1%88%AA/

አዲስ አበባ፣ የካቲት5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተጠርጣሪውን በእባብ ያስፈራራው መርማሪ ፖሊስ ይቅርጣ ጠየቀ፡፡

መርማሪ ፖሊሱ ይቅርታ የጠየቀው ተጠርጣሪውን በእባብ በማስፈራራት መረጃ ሲውጣጣ የሚያሳይ የምስልና ድምጽ መረጃ በማህበራዊ መዲያዎች ከተለቀቀ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በኢንዶኔዥያ የጃያዊጃያ ዋና ፖሊስ አዛዥ ቶኒይ አናንዳ ሳዋዳያ ፖሊሱ ይህን ድርጊት መፈጸሙንና ይቅርታ መጠየቁን አረጋግጠዋል፡፡

መርማሪው ድርጊቱን የፈጸመውም በራሱ ተነሳሽነት ሲሆን÷ የሀገሪቱ የፖሊስ የሙያ ስነ መግባር የማይፈቅደው ተግባር ማካናዎኑንም የፖሊስ አዛዡ አስረድተዋል፡፡

የፓፑዋ ፖሊስ ቃል አቃባይ አህምድ ሙስጦፋ ካማል በበኩላቸው የምርመራ ሂደቱ የሙያ ስነ ምግባር መጣሱ ከተረጋገጠ ድርጊቱን በፈፀመው ፖሊስ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡

በፓፑዋ አካባቢ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በፀጥታ ኃይሎች የሰባዊ መብት ጥሰት በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም ዘገባው ያመለከታል፡፡

መርማሪ ፖሊስ እጆቹ ወደ ኋላ የታሰሩ ግለሰብ እባብ በአንገቱ ላይ በማድረግ መር መሪው መረጃ ሲውጣጣውና ቃሉን ሲቀበል እንደነበር በማህበራዊ ሚዲየዎች ሲዘዋወር ከነበርው የምስልና ድምጽ መልዕክት መረዳት ተችሏል፡፤

ተጠርጣሪው ሞባይል ስልክ በመስረቅ የተጠረጠረ ሲሆን÷ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው አንገት ላይ የተጠመጠመውን ከእነ ነፍሱ ያለ እባብ ወደ አፉ ባመስጠጋት እስካሁን ስንት የእጅ ስልኮችን ሰርቀሃል እያለ ሲጠይቀው መሰማቱም ነው የተነገረው፡፡

በዚህ እባብ ከፍተኛ ፍራት ያደረበት ተጠርጣሪው ሁለት ስልኮችን ብቻ ሰርቄያለሁ ሲል መሰማቱን ካላይ ከተገለጸው የምስልና ድምጽ መልዕክት ተገኝቷል ተብሏል፡፡

መርማሪው እባቡን ወደ ተጠርጣሪው አፍ ሲያስጠጋ ተጠርጣሪው አይኑን ይጨፍን ስለነበር መሪማሪው አይኑን እንዲገልጥ ያስገድደው እንደነበረም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህም ሌላ ይህንኑ እባብ በተጠርጣሪው ሱሪ ውስጥ ሲያስገባበት እንደነበረም ነው የተነገረው፡፡

ይሁን እንጅ እባቡ የማይናዳፍ እና መርዝ የሌለው እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡

በተጠርጣሪው ላይም አካልላዊ ጉዳት እንዳልደረበትም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሬውተርስ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.