ቱርክ ለሊቢያ ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%89%B1%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%88%88%E1%88%8A%E1%89%A2%E1%8B%AB-%E1%8B%88%E1%89%B3%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%8B%8A-%E1%8B%B5%E1%8C%8B%E1%8D%8D-%E1%88%8D%E1%89%B3%E1%8B%B0%E1%88%AD%E1%8C%8D-%E1%8A%90/

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ለሊቢያ ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው።

አንካራና ትሪፖሊ ባለፈው ወር በወታደራዊ መስክ ትብብር ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

አሁን ይደረጋል የተባለው ድጋፍም የዚህ ስምምነት አካል ሲሆን፥ ድጋፉ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ በፓርላማው መጽደቅ ይኖርበታል።

አንካራ የምታደርገው ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ለተሰጠውና መቀመጫውን ትሪፖሊ ላደረገው አስተዳደር ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሜቭሉት ካቩሶግሉ ድጋፉ በፓርላማው ከፀደቀ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ባላፈው ሃሙስ ተቀናቃኙ ከሊፋ ሃፍጣር ወታደሮቻቸው ትሪፖሊን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።

 

ምንጭ፦ ሬውተርስ

 

 

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.