ቱርክ በሰሜን ሶሪያ የከፈተችው ከባድ ወታደራዊ ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%89%B1%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%88%B0%E1%88%9C%E1%8A%95-%E1%88%B6%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%8A%A8%E1%8D%88%E1%89%B0%E1%89%BD%E1%8B%8D-%E1%8A%A8%E1%89%A3%E1%8B%B5-%E1%8B%88%E1%89%B3/

አዲስ አበባ፣ መስከረም29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ቱርክ በሰሜን ሶሪያ በኩርድ ታጣቂዎች ይዞታ ስር የከፈተችው ከባድ ወታደራዊ ዘመቻ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል፡፡

ጥቃቱ በአየር እና በምድር ጦር የታገዘ ሲሆን÷ የቱርክ መከላከያ ስትራቴጅክ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

አሁን ላይ በሰሜን ሶሪያ እና ደቡብ ቱርክ አዋሳኝ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

በጦርነቱ የሰባት ንጹኃን ዜጎች ህይወት ሲያልፍ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መኖሪያቸውን ለቀው ወጥተዋልም ነው የተባለው፡፡

ቱርክ ወታዳራዊ ዘመቻውን በኩርድ ታጣቂዎች ላይ የከፈተችው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ጦር ከአከባቢው የማስወጣት ውሳኔ ተክትሎ መሆኑ ይነገራል፡፡

የኩርድ ታጣቂዎች በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት በአሜሪካ ድጋፍ ከኤስ አይ ኤስ ቡድን ጋር ሲፋለሙ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡

ይሁን እንጅ ቱርክ የኩርድ ታጣቂዎችን በሽብርተኝነት ፈርጃለች፡፡

የዘመቻው ዓለማም ቀጠናውን ከሽብር ነፃ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ቱርክ አስታውቀለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዙሪያ እየመከረ ነው፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት የአስቸካይ ስብሰባ የጠራው በብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ ቤልጂየም እና ሆላንድ ጥያቄ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.