ታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ የዐማራ ህዝብ የነጻነት ፋና ወጊ ከተሰዋ አንድ ዓመት ሞላው

Source: http://welkait.com/?p=12659

አርበኛ ጎቤ መልኬ

የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ ሲኖር ከሐብት፣ ከንብረትና ከምቾች ይልቅ ያለነጻነት መኖር እንደማይችል ታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ ህያው ምስክር ነው።ታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ በታች አርማጭሆ ወረዳ በአካባቢ ህዝብ ዘንድ የተከበረ አራሽ-ነጋዴ፣ ነበር። ታጋይ አርበኛ ጎቤ አራት የጭነት አይሱዚ መኪኖች፣ ከአራት መቶ በላይ የቁም ከብቶች፣ በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረትና ሰፊ የሰሊጥ እርሻ መሬት ባለቤት፣ ከነጻነት በቀር ምንም ያላጣ ታዋቂና የተከበረ ሀገርና ወገን ወዳድ ባለሃብትና ጀግና ነበር።

ታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ ዘረኛው የትግራይ ወያኔ በወገኑ ላይ እያደርሰ ያለው ግፍና መከራ የሰው ልጅ ከሚችለው አቅሙ በላይ መሆኑ በማየቱ ሃብትና ንብረቱ ጥሎ ወደ ትግል ሲገባ ገድሎ ሊሞት እንደሆነ ከመጀመሪያውም አውቆ የገባበት ትግል መሆኑን ያውቀዋል።

የታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ መሰዋዕት ሆኖ ማለፍ የተጀመረውን የነጻነት ትግል ወጣቱ የአማራ ትውልድ አጠናክሮ እስከ ነጻነት ድረስ እንዲታገል የበለጠ ጉልበት ይሰጠዋል እንጃ ለአንድ ደቂቃም ቢሆን አያቆመውም።

ወጣት የአማራ የነጻነት ታግዮች የአባታችን የታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ በማንገብ ወደፊት እስከ ነጻንት ድረስ እንቀጥላልን።

ዘላለማዊ ክብር እየተደረገ ላለው የነጻነት ትግል ውድ ህይወታቸው ለከፈሉ ለታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬና ለአማራ የነጻነት ታጋዮች በሙሉ!!

ከዚህ ቀጥሎ የዐማራ ድምጽ ራዴዮ  የአርበኛ ጎቤ መልኬ መሰዋት መሆን አስመልክቶ “ጀግና ብርሌ ነው” በሚልስ ርዕስ ያወጣውን አጠር ያለ ዘገባ አዳምጡ።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.