ትናንት ምሽት በአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ላይ የተፈጸመው ተግባር ተቀባይነት የሌለውና ስህተት ነው – አቶ ሽመልስ

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%89%B5%E1%8A%93%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%9D%E1%88%BD%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%89%B2%E1%89%AA%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8C%83%E1%8B%8B%E1%88%AD-%E1%88%98%E1%88%83%E1%88%98%E1%8B%B5/

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት የአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎችን ለማንሳት የተፈጸመው ተግባር በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለውና ስህተት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

አቶ ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ድርጊቱ በመንግስት የማይታወቅ ከመሆኑ ባሻገር በዚህ ጉዳይ የተሳተፉ አካላት ላይ ማጣራት ተደርጎ እርምጃ እንደሚወሰድና ለህብረተሰቡም ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ጃዋር ጥበቃ ሲደረግለት የነበረው በመንግስት ታምኖበትና በምክንያት መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁንም በነበረው መሰረት እንደሚቀጥልና የተቀየረ ውሳኔ እንደሌለም ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች በተደረገው ሰልፍ ህብረተሰቡ ትክክለኛ ስሜትና ጥያቄውን አቅርቧል ያሉት አቶ ሽመልስ፥ አንዳንድ ልዩ ተልዕኮ ያላቸው አካላት ግን ተቀላቅለው በንብረት ላይ ውድመትና ዘረፋ ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋልም ነው ያሉት።

እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ መንቀሳቀሳቸውንም አንስተዋል።

የሃገር ሽማግሌዎች ወጣቱና በአጠቃላይ ነዋሪው ይህን በማረጋጋትና የፀረ ህዝብ ተልዕኮዎች ግባቸውን እንዳይመቱ ላደረጉት ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ለድል የበቃውና ፈተናዎችን ያለፈው በአንድነትና በትብብር በጋራ በመቆሙ መሆኑን ጠቅሰው፥ ዛሬም ይህን ትልቅ ሃብቱን እንዲንከባከብና ተግባር ላይ እንዲያውልም ጠይቀዋል።

የተፈጠረው ስህተት እንዳይደገም እንደሚሰራና አክቲቪስት ጃዋር በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አውስተዋል።

ህዝቡም ተረጋግቶ ሰላሙን እንዲያስከብርም ጥሪያቸውን አቅርበው፥ ለተጎዱ ወገኖችም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

Share this post

One thought on “ትናንት ምሽት በአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ላይ የተፈጸመው ተግባር ተቀባይነት የሌለውና ስህተት ነው – አቶ ሽመልስ

  1. Comment: juhar’s father was frmo yemen, as such he is a terrorist as binladen alqaida, he is an agent of egypt against ethiopia. We need to treat him as isis.
    The problem is that odp especially lema megersa, shmels and uula gemeda are behind him.
    They must be treated as criminals and traitors

    Reply

Leave a Reply to Bel Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.