ትዝብት [፩] – ከአቻምየለህ ታምሩ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81231

ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ጀምሮ እስካሁንም ድረስ እንደቀጠለ ያለው የምስራቅ ኢትዮጵያ «ችግር» ወያኔ የፈጠረው እንጂ በቋንቋ ላይ የተመሰረተው «የብሔር ፌድራሊዝም» የወለደው እንዳልሆነ ለማሳየት በጎሳ ብሔርተኞች ዘንድ ያልተፈነቀለ ድንጋይና ያልተማሰ ጉድጓድ የለም። ሶማሌና ኦሮሞ ባህልና ቋንቋ እንደሚጋራ፤ የረጅም ዘመን ጉርብትና እንዳላቸው፤ እንደተጋቡና እንደተዋለዱ፤ ወዘተ እየተጠቀሰ የተፈጠረው ግጭት የወያኔና ያብዲ ኢሌ ስሪት እንጂ «የብሔር ፌድራሊዝሙ» የወለደው የጎሳ ግጭት […]

Share this post

One thought on “ትዝብት [፩] – ከአቻምየለህ ታምሩ

 1. …”የሶማሌ ክልል መስተዳደር ባወጣው መግለጫ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ለተፈጠረው ግጭት መነሻ ያላቸውን አራት ምክንያቶች በዝርዝር ገልጿል፡፡ የተጠቀሱት ምክንያቶች በጣም አስገራሚ ከመሆናቸው በላይ በፌዴራል ስርዓት ላይ የተጋረጠውን አደጋ በግልፅ ይጠቁማሉ፡፡ በአጠቃላይ መግለጫው የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በግጭቱ ዙሪያ ያላቸውን አቋምና አመለካከት በግልፅ የሚያሳይ ሆኖ ስላገኘነው በመግለጫው የተዘረዘሩትን ምክንያቶች የተወሰኑ የቃላትና አፃፃፍ ግድፈቶችን በማስተካከል እንደሚከተለው አቅርበንዋል፡፡ ሙሉ መግለጫውን ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ፡፡

  የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስትና አገር ሽማግሎች በኦሮሚያ ጥቃት ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ይፋ አደረጉ፡፡ጅግጅጋ (Cakaaranews) መክሰኞ መስከረም 23/ 2010 ዓ.ም፡፡…በመድረኩ ላይም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራርና የክልሉ አገር ሽማግሎችም ተገኝቷል፡፡ የክልሉ መንግሰት አሮሚያ በኢትዮጵያ ሶማሌ ላይ በቋሚነት የሚታወጃው ተከታታይ ጦርነት መንሰኤዎች እንደሚከተለው ገልፀዋል፡-

  (፩)ኦሮሚያ የኢትዮጵያ ሶማሌ መሬት በኃይል ለመወሰድና ከጎሮቤት አገራት እንደ ሶማሊላንድና ሶማሊያ ጋር ግንኙነት በመፍጠርና እንደሁም የጎሮቤት አገራት ወደብ በመጠቀም ኢትዮጵያ የሚያፈራረሱበት ጦር መሳሪያ ለማስገባት ሲሆን በአሮሚያ ሴራ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ከባድ ማቀብ ስለሆነበት ነው፡፡
  (፪)የኦሮሞ ጦርነት በስተጀርባ ያለው ምክንያቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልልን የፈጠረ ሰላምና ማረጋጋት እንደሁም በሻቢያ የጋራ መቀመጭያ የነበሩት ፀረ-ሰላም ኃይሎች እንደ አልኢተሓድ፣ አልኢጃራ፣ ኦቦ (ኦብነግ)፣ ኦነግና የመሳሰሉት ፅንፈኞች ኤርትራ የሚትሰጠው ጦር መሳሪያዎችን በአንድ ጀልባ ሲትላክላቸው ስለነበርና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ስለተደመሰሱና የጦር መሳሪያዎች ማስገባቱ ስለታገደባቸው በኦሮሚያ ክልል ላይ ቁጭት ስላሳድባታል።
  (፫) የኦሮሞ ጦርነት ምክንያቱ ደግሞ በቅርቡ አሮሞችሁ ሌላ ሸሚዝ በመልበስ የአዲስቷ ኢትዮጵያ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ሰጥታና ልማትን ያጎፀፈው ኢህዴግን በቀላሉ ለመቀልበስና የፈዴራሊዝም ሥርዓትና የህግ የበላይነትናን ለመተራመስና አንባገነኑ የደርግ ሥርዓት ለማስመለስ ኦሮሚያ እያደረገች የነበረው ቀውስና ብጥብጥን በኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብና መንግስት ስለተወቀሱ ነው፡፡ ከዚህ በተያያዜም የክልሉ መንግስት ኢትዮጵያነታችንም ከማንም ጀርባ ሆነን አንለምንም ብሏል፡፡
  (፬) ከአሁን በፊት በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች እና ዞኖች ለመሄድ በሌላ ክልል ተቋርጦ ከረጅም ጉዞ በኋላ ሲደርሱ የነበሩ የክልሉ ወረዳዎችና ዞኖች በክልሉ መንግስት በአጭር ግዜ ውስጥ የተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ልማትን በተላይ መንገድና ድልድዮች በመገንባትና ሁሉም የክልሉ ወረዳዎችና ዞኖች በማስተሳሰሩ፣ ከሌላ ክልል መዞሩ በክልሉ መንግስት ማቅረፉ በኦሮሚያ መንግስት ላይ ቁጭት ስለፈጠርበትና በተላይ በመንገድ መስረተ ልማት እጥረት በኦሮሚያ ክልል ተቋርጦ ሲገኝ የነበሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወረዳዎች እንደ ለጋሂዳ፣ ሰለሃድ፣ ቁቢ፣ መዩሙሉቆ፣ ቀርሳዱላ እና ፊልቱ ወረዳዎች ከክልሉ ዋና ከተማ በመንገድ መስረተ-ልማትና በትላልቅ ድልድዮች ከማስተሳሰሩ ባሻገር የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት በጥቂት አመታት ውስጥ በክልሉ ያከናወናቸው ትላልቅ የውሃ ማቆሪያዎችና ሜጋ የመስኖ ግድቦችሁ ለግብሪና ምርትና ምርታማነትን ስለሚያገለገሉና ከኦሮሚያ ሲቀርብ የነበሩ አትክልትና ፊራፍሬዎችሁ በሶማሌ ክልል ገበያ እንዳይኖቸው የአሮሚያ ክልል መንግስት ለሶማሌ ገበያ የሚየቀረርቡት ምርት ትልቅ ስጋት ስለሆነበት የኦሮሚያ ጦርነት አንዱ ምክንያት ተብሏል፡፡
  ***************!
  የጀዋሪያን የሜንጫ አብዮት “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!” ኢትዮሱማሌውን አደለምን?ፀጋዬ አርአንሳ የምንይልክ ሠፋፊ ፡ መጤ “ሲል መርካቶ ሱማሌ ተራ ሕዝብ መናቁ አደለምን? ለመሆኑ ያንቆለጳጰሠው ፌደራሊዝም እና ያስተማረው ሕገ መንግስት ሕዝቤ የሚለውን መጤ አድርጎ ሕፃናትን አዛውንትና እናቶችን እንደከብት ሲታጨቁ ሲያይ ደስ አለው ?ሱማሌና ኦሮሞ አንድ ናቸው !?ፀቡ የግጦሽ መሬት እንደጥንቱ ከሆነ ለምን ተፈናቀሉ ?ይህ ሁሉ ከብት አርቢ ከሆኑ ከብቶቹ የት ገቡ!?” ክልል ማለት ሀገር “ብለው ጫካ ስለተማማሉ ሕገመንግሥታዊ የዜግነት ጥበቃ/ከለላ ስለሌለ የባሪያ አሳዳሪው ሕወሓት ስትፈልጉኝ ብቻ እመጣለሁ ብሎ በሜንጫ ሲተላለቅ ይስቃሉ ፡ የዲያስፖራው ነፃ አውጭ ጥሩንበኛ ቱልቱላ እሬሳ ቁስለኛ ተፈናቃይ ቆጠራ ላይ ይላፋል። በራስህ እንዲደርስ የማትፈልገውን ጭካኔ ለሌላው አትመኝም ብድር በምድር ነውና ዱልዱም ቦልጥቀኞች መሞጣሞጣቸውን ያቁሙ ።አራት ነጥብ።

  Reply

Post Comment