ቻይና ውስጥ የታተመው ‹‹መደመር›› የተሰኘው የጠ/ሚ አብይ መፅሀፍ ገበያ ላይ ሊውል ነው።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/157087

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፃፉት ‹‹መደመር›› የተሰኘው መፅሀፍ በዚህ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ ተሰምቷል!
ካፒታል የእንግሊዘኛ ጋዜጣ እንደዘገበው መፅሀፉ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን 287 ገፆች ያሉት ነው፡፡ የመፅሀፉ አንድ ሚሊዮን ኮፒ በቻይና በነፃ እንደታተመም ጋዜጣው አስረድቷል፡፡
16 ምእራፎች ያሉት መፅሀፉ አገሪቱ መከተል በሚገባት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የውጭ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የፖሊሲ ጉዳዮችን የያዘ ነው ተብሏል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ታዛቢዎች የዚህ መፅሀፍ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ገዢው ፓርቲ ወደፊት የሚከተለው ርእዮተ አለም እንደሚሆን እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ እስካሁን ድረስ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ እየተመራ ያለው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ባረቀቁትና አብዮታዊ ዲሞክራሲ በተሰኘው ርእዮተ አለም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ይህ ‹‹መደመር›› የተሰኘው መፅሀፍ ለገበያ የሚቀርበው በ300 ብር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከሽያጩ የሚገኘው ገቢም በአገሪቱ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ለማሰሪያነት እንዲውል መታሰቡም ተሰምቷል፡፡ መፅሀፉ በእንግሊዘኛ የቀረበው ‹‹ሲነርጂ›› በሚል ርእስ ነው፡፡
Via Abdurahim Ahmed
Image may contain: 2 people

Share this post

One thought on “ቻይና ውስጥ የታተመው ‹‹መደመር›› የተሰኘው የጠ/ሚ አብይ መፅሀፍ ገበያ ላይ ሊውል ነው።

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.