ኃላፊነት የጎደላቸው ሚዲያዎች በተማሪዎች ላይ ስጋት እንዲያድር ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/170978

አሳማኝ ምክንያት የለሽ ስጋት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያወከ መሆኑ ተገለጸ፡፡
(አብመድ) በምክንያት አልባ ስጋት የፀጥታ ችግር በሌለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው የመመለስ ፍላጎት እንዳሳዩ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ ኃላፊነት የጎደላቸው ሚዲያዎች በተማሪዎች ላይ ስጋት እንዲያድር ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን በዩኒቨርሲቲው ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ተናግራል፡፡ የተቋሙን ሠላም ለማወክ የሚሠሩ አካላት መኖራቸውን ያመላከቱት ዶክተር አስራት የፀጥታ አካላቱ ይህንን በመረዳት በንቃት እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በቅርቡም ከተማሪዎች ጋር ተቀላቅለው ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት የፀጥታ ችግር ሊፈጥሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር በትጋት እየተሠራ መሆኑን ነው ዶክተር አስራት የተናገሩት፡፡

ምንም እንኳን በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ባይፈጠርም ከኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉ ተማሪዎች በስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ግን ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስ በማግባባት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎችም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ተማሪዎችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ የፀጥታ አካላት የተጠናከረ የጥበቃ ሥራ እያከናውኑ እንደሚገኙ ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ያስታወቁት፡፡
በተማሪዎች ዘንድ በተፈጠረው ስጋት ምክንያት ከአምስቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢዎች መካከል በአንዱ ሙሉ በሙሉ፤ በሁለቱ ደግሞ ደግሞ በከፊል ትምህርት ተቋርጧል፡፡ የተፈጠረውን ስጋት በማስወገድ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ‹‹ተማሪዎች በውይይቱ ችግር ሊከሰት ይችላል ከሚል ስጋት የተነሳ ዩኒቨርሲቲውን ለቅቀው ለመውጣት ማሰባቸውን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.