ነገና ከነገ በስተያ በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ምክንያት በመዲናዋ ዝግ ሆነው የሚቆዩ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል

Source: https://fanabc.com/2018/11/%E1%8A%90%E1%8C%88%E1%8A%93-%E1%8A%A8%E1%8A%90%E1%8C%88-%E1%89%A0%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%88%85%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%8C%89%E1%89%A3/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2011(ኤፍቢሲ) የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በሚል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡

የመሪዎቹ ጉባዔ ህዳር 8 እና 9 የሚካሄድ ሲሆን፥ በርካታ እንግዶች ጉባዔውን ለመታደም አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

በዚሁ መሰረት ፖሊስ ኮሚሽኑ ይፋ ካደረጋቸው መንገዶች መካከል ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ ኦሎምፒያ ወሎ ሰፈር ጃፓን ኤምባሲ ፍሬንድ ሺፕ ቦሌ ቀለበት መንገድ ኤርፖርት አንዱ ነው፡፡

እንዲሁም ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በብሄራዊ ቤተመንግስት በፍልውሃ ብሄራዊ ቴአትር ሜክሲኮ አደባባይ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ሌላኛነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከፓርላማ መብራት በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን መሆኑን ገልጿል፡፡

ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለባቸው መስመሮች ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ከአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዛሬ ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ አማራጭ መንገዶችን በተመለከተ ይፋ ካደረጋቸው ከጦር ሃይሎች  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ መስቀል አደባባይ አቋርጠው  ወደ መገናኛ ለሚሄዱ  ተሽከርካሪዎች፦

በኮካኮላ ድልድይ በአብነት ተ/ሃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ ወይንም በኤክስትሪም ሆቴል ቴዎድሮስ አደባባይ አሮጌ ቄራ አንደኛው ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ በባልቻ ሆስፒታል አረቄ ፋብሪካ ጎማ ቁጠባ ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ኦርማ ጋራዥ በንግድ ማተሚያ አሮጌ ቄራ በኩል መሄድ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚሄዱ ተሸከርካሪዎች ሳር ቤት ጎፋ ማዞሪያ ቄራ ጎተራ ጎርጎሪዎስ ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ መጓዝ ይችላሉ ብሏል፡፡

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ ዘሪሁን እንዲሁም በቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ በተጨማሪም በቀለበት መንገድ መገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ ወይንም በቀለበት መንገድ መገናኛ አድዋ ጎዳና አዋሬ አራት ኪሎ እና ከፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አስታውቋል።

በተጨማሪም ከፓርላማ እስከ ቦሌ አፍሪካ ህብረት ዙሪያ ምንም አይነት ከባድ ተሽከርካሪ ወደ አጀብ መስመሩ መግባት ፍፁም ክልክል መሆኑን ኮምሽኑ ጨምሮ ገልጾ፥ መንገድ ተጠቃሚ እግረኞችና አሽከርካሪዎች የሞተረኛ የትራፊክ የእሳት አደጋ የአምቡላንስ ሳይረን ድምፅ ሲሰሙ ቀኛቸውን ይዘው በማቆምና በማሳለፍ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አሳስቧል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.