ነፍጠኛ! – በላይነህ አባተ

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107650

ስጋህን አድርገህ ጣራ አጥንትህም ወጋግራ፣ የአለት መሰረት አንጥፈህ የአገር አዳራሽ ብትሰራ፣ ዋው! ዋው! እያሉ ነከሱህ አብዶ እንደሚለክፍ ቡችላ፡፡ ደምህን እንደ ወንዝ አፍሰህ ድንበር ጠብቀህ ስለኖርክ፣ በደቆስካቸው ባእዳን የተንኮል አውታር ተጠልፈህ፣ በእነሱ አምላኪ ባንዳዎች በጥርስ በድድ ተነክሰህ፣ አንበሳው እንቅልፍ ሲይዝህ ጆፌዎች ኩስን ጣሉብህ! ወርቁን በሰም ሸፍነህ ስለጋትክ የቅኔ ዘመራ ብርዝን፣ ቀለምን ጨምቀህ ተእጸዋት ቆዳውን ፍቀህ ብራናን፣ ተዓለማት በፊት ስለቻልክ ጥበብን መጣፍ ማንበብን፣ በቅናት ሰክረው ዶለቱ ሲያጠፉት ታሪክ ቅርስህን፡፡ ተፈጥሮን ዓይተህ ስዕሉን መጣፍ መርምረህ ጥበብን፣ ድንጋዩን ፈልጠህ ቤተክሲያን መሬት በርቅሰህ ጤፍ ምርትን፣ ስትመግብ በኖርክ ዓለምን ሌሎች ሲለቅሙ ዛፍ ፍሬን፣ ዝቅ ያለ መንፈስ ነዳቸው እንደ ገለባ አርጎ ብን፡፡ ጊዜን በቀመር ለክተህ ዓመቱን በወር

The post ነፍጠኛ! – በላይነህ አባተ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.