ንግድ ሚኒስቴር ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው አሳሰበ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/53714


ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ በመረጋገጡ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውለው የንግድ ሚኒስቴር አሳሰበ።
የሚኒስቴሩ የገበያና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት እንደተናገሩት፥ በላይ ኢንዱስትሪያል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚያመርተው ክላሲ የታሸገ ውሃ በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከ2007 እስከ 2009 ዓመተ ምህረት በተደረገ የጥራት ፍተሻ ምርቱ በተደጋጋሚ የጥራት ጉድለት የታየበት በመሆኑ እንዲታገድና ከገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉንም ነው ዳይሬክተሩ ያስታወሱት።
ድርጅቱ የምርት ጥራቱን እንዲያስተካክል የውዴታ ግዴታ እንዲፈርም በመደረጉ ማስተካከሉ ተረጋግጦ ታህሳስ 2009 ዓ.ም እገዳው ተነስቶለት ወደ ስራ ገብቷል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.