አህያዬን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊዬ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/133299

አህያዬን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?ይህ አባባል ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብሎሽ እየተሻገሩ ዘመን ካቌረጡት ከብዙ ክስተቶች አንዱ እንደሆነ አበው ይናገራሉ።
እኛ የኦርቶዶክስ ይማኖት መምህራን፤ “ለትውልደ ትውልድ ዘኢየኀልቅ ለዓለም ዓለም” ብሎ በሚደመድመው በየመንፈቀ ሌሊት በምናደርሰው  ጸሎተ ኪዳናችን  ትንሹንና ትልቁን ህዳጡንና መንጋውን ህብረተሰቡን አጠናቅሮ  በመምራት ላይ ያለውን ተወራራሽ  ምድራዊ መንግሥት እንቃኝበታለን። በአመጽም ሆነ በሰላም ቅብብሎሽ እየተፈራረቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ በመሻገር ላይ ያለው ምድራዊና ጊዜአዊ መንግሥትም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት እንደሚዋጥ እናስተምራለን።
ኢትዮጵያውያን መተርጉማን ይህን ሐረግ ከመሳሰሉት ምንባባት በመነሳት፤ እንደ እኛ በቅኝ ግዛት ሳይወረር በኖረ  ሕብረተ ሰብ የሚነገሩት በብራና ባይጻፉም ተረቶች ወይም ፈጠራዎች አይደሉም። ባንድ ትውልድና ዘመን ተከስተው ዘመናትን  እየተሻገሩ በቅብብሎሽ የመጡ ናቸው“ እያሉ ነግረውናል። ”አህያየን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊየ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?የሚለው ክስተት  በጽሑፍ ባይቀረጽም በቃል ንግግር ቅብብሎሽ በየትውልዱ የሚደርስ ነው። ይህን የመሳሰሉ ክስተቶች ከረዥም ዘመን በኋላ ባዲሱ ትውልድ ላይ ሲወድቁ፤ አዲሱ ትውልድ ለመቀበል  እየከበደው ተረት ይመስሉታል።  ግን ቅርጻቸውን፤ ይዘታቸውንና ትርጉማቸውን እየቀያየሩ በየትውልዱ የሚከሰቱ አማናውያን ናቸው ይላሉ።
 “ለትውልደ ትውልድ ዘኢየኀልቅ ለዓለም ዓለም” በሚለው ምንባብ ላይ የተመሰረተው ሐተታ እንደሚጠቁመን፤  ቀዳማዊው መንግሥት በደሀራዊው መንግስት እየተዋጠ በሚሻገር እንደ ኢትዮጵያ በመሰለ ኅብረተሰብ የሚነገሩ አፈታሪኮች ካለፈው ትውልድ አካል ጋራ አይቀበሩም።  ከማይቀበረው  ታሪክ ጋራ በትኩረት ሊጠኑንና ሊመረመሩ የሚገባቸው ናቸው። የቀደሙ አባቶቻችን በግል አካላቸው በመቃብር ቢወሰኑም፤ ባወረሱን አካላቸውና በሰሩት ታሪካቸው በነገሩን ትንግርታቸው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.