አልጄሪያ ሁለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮቿን አሰረች

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%8C%84%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E-%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AE/

አዲስ አበባ፣ህዳር 30፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አልጄሪያ ከሙስና ክስ ጋር በተያያዘ ሁለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮቿን አሰረች፡፡

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተከሰሱትን ከባድ የሙስና ወንጀል ሲመረምር የቆየው የአልጄሪያ ፍርድ ቤት ÷አህመድ ኦይሃን በ15 ዓመት አብዱልመላክ ሴላል በ12 ኣመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

በገንዘብ ማጭበርበር፣ስልጣንን ያላግባብ በመጠቀም እና በመኪና ኢንዱስትሪ ውስጥ ተገቢ  ያልሆነ ጥቅም በማግኘት  ከተከሰሱ  19 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ ባለስልጣናት ይገኙበት እንደነበረ ተገልጿል፡፡

አልጄሪያ በ1962 ከፈረንሳይ ነጻነቷን ካገኘች ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ ባለስልጣናትን ፍርድ ቤት ስታቀርብ ይህ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል፡፡

ሁለቱ ባለስልጣናት በሚያዝያ ወር በተካሄደው ህዝባዊ አመጽ ከስልጣናቸው የለቀቁት የፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቦትፊሊካ አጋሮች ነበሩ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.