አማራዊ ማንነትንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማፅዳት ዘመቻዎች እንዲቆሙ አማራ የሆነ ሁሉ በየአካባቢው በመደራጀት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠትና መመከት እንደሚጠበቅበት የአ…

አማራዊ ማንነትንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማፅዳት ዘመቻዎች እንዲቆሙ አማራ የሆነ ሁሉ በየአካባቢው በመደራጀት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠትና መመከት እንደሚጠበቅበት የአ…

አማራዊ ማንነትንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማፅዳት ዘመቻዎች እንዲቆሙ አማራ የሆነ ሁሉ በየአካባቢው በመደራጀት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠትና መመከት እንደሚጠበቅበት የአማራ ወጣቶች ህብረት በባህር ዳር አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ህብረት በባህር ዳር ዛሬ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አማራዊ ማንነትንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማፅዳት ዘመቻዎች እንዲቆሙ አማራ የሆነ ሁሉ በየአካባቢው በመደራጀት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠትና መመከት እንደሚጠበቅበት ነው ያሳሰበው። በአማራ ህዝብ ላይ በየአቅጣጫው በተቀናጀ እና በተጠና አካሄድ በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉ የዘር ማጥፋትና ማሳሳት የወንጀል ድርጊቶች አማራን እንደ ጨቋኝ ከሳሉበት የሀሠት ትርክትና ጥላቻ እንዲሁም ከዝቅተኝነት ስሜት እንደሚቀዳ የገለፀው ህብረቱ የ1960ዎቹ ፖለቲከኞች እና ቡድኖች እስከ ዛሬም ድረስ በየመድረኩ የሚያላዝኑት፣በሙዚቃቸው፣በለቅሷቸውና በየቡና ቤቱ የሚሰብኩት የአማራ ጥላቻን ነው ብሏል። ይህን አይዲዮሎጂና አመለካከት ከ50 አመት በኋላም መንግስት የሆኑት አካላት እንኳን ለመቀየር ፍላጎት አለማሳየታቸው እና አለመረዳታቸው እንዳሳሰበው የጠቀሰው የወጣቶች ህብረት በዚህ ሁሉ ጊዜ በግትር አቋማቸውና አሉታዊ አመለካከታቸው በአማራ ህዝብ ላይ የወረደውን መዓት ከማስቆም ይልቅ የእሬሳ ብሔር አትቁጠሩ በማለትና በማስተባበል በመልካም እንዲዘከርላቸው የሚሹ ሀይሎች ሁነው ቀጥለዋል ነው ያለው። የዝቅተኝነት ስሜት አረመኔ ያደረጋቸው ፈጣሪን የማይፈሩ ዘላኖች የመንግስትን ድጋፍ መከታ በማድረግ በአራቱም አቅጣጫ እሬሳ ማስቆጠራቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል ሲልም አክሏል ማህበሩ በመግለጫው። በመንግስት ደረጃ አማራ ላይ ሁለንተናዊ ጫና ለማድረስ እንደዋና መሠረት የተጠቀሙበት አማራውን ርስት አልባ ማድረግ፣ ግዛቶቹን ከፋፍሎ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱንና ድምፁን ማኮስመን ስትራቴጅ እንደሆነ የጠቀሰው የአማራ ወጣቶች ህብረት በባህር ዳር የጦር ስልት በመንደፍ አማራን በመግደልና በማፈናቀል የህዝብ ቁጥር ተዋፅኦን የማሳነስ፣ የህዝብ ቁጥርን የማሳሳትና ዘርን ማጽዳት የጦረኝነት ስልትን ነድፈው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስታውቋል። ይህ አካሄዳቸውም ከጣሊያን ተኮርጆ በተለይም ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በመንግስት ደረጃ ተፈፃሚ በመሆኑ ህዝባችን በርካታ ችግሮችን እያስተናገደ እንዲኖር አድርጎታል ሲልም አክሏል። አማራው የኢትየጵያን ህዝብ ከስልሳ ፐርሰንት(60%) በላይ መሆኑን የጠቀሰው ማህበሩ በድፍረት፣ በተገላቢጦሽ እና በመንግስት በታገዘ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ጭምር እኛ ከፍተኛ ቁጥር አለን ከማለት አልፈው እናንተ መጤ ናችሁ ሀገራችንን ልቀቁ እስከማለት ደርሰዋል፤ በመሆኑም ይህን አካሄድ ከዚህ በኋላ ዝም ብለን ቁመን የምንቀበለው አይሆንም ነው ያለው። አማራን ለማጥፋት የተነሳው መንግስታዊ ቡድን የህዝብ ቁጥር የማሳነስን ስትራቴጅ ለመቀየስ አፋርን በሌላ አደረጃጀት በመነጠል፣በአማራው ላይ የውስጥ ክፍፍልን በመፍጠርና በመደገፍ በተለይ ህዝቡን ከእነ መሬቱ ከሌላ ብሔር ጋር በማካለል እና ውክልና በመንፈግ ቃፍቲያ፣ ሁመራን፣ ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ጠለምትን፣መተከል ዞንን፣መላ ራያን፣ ደራን እና መላ ሸዋን ቀስ በቀስ የመጨፍለቅና ዲሞግራፊ የመቀየር ስራ ሰርቷል ብሏል። የተንኮልና የመከፋፈል ሴራው ተፈፃሚ እንዲሆንም በየክልሎቹ በመንግስትና በፀጥታ አካላት በታገዘ ዘመቻ ነባሩን የአማራ ህዝብ ማህበራዊ እረፍት የሚነሱ ስውር አደረጃጀቶችን እንደአብነትም ህወሀትን፣ኦሮሙማንና የጉምዝ ተወላጆችን እንደ መሳሪያ በመጠቀም አማራው በአባቶቹና በራሡ እርስት በግፍ ተደብድቧል፣ቤቱና ንብረቱ ተቃጥሏል፣አማርኛ እንዳይናገር ተከልክሏል፣በታጠቁና በተደራጁ ሀይሎች አማራው እራሱን እንዳይከላከል በመንግስት ተከልክሎ፣ ጥበቃ ሳይደረግለት እንዲሞት ተፈርዶበታል ሲል በመግለጫው አስፍሯል። ፀረ አማራዎች በመንግስት ተደግፈው ክፉ አላማቸውን ለማሳካት ሲሉ በአማራ ህዝብ ላይ በየአቅጣጫው በተቀናጀ እና በተጠና አካሄድ በየጊዜው ማንነትንና እምነትን መሠረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማፅዳት ዘመቻዎችን እየፈፀሙ መሆናቸውን የጠቀሰው የአማራ ወጣቶች ህብረት በባህር ዳር ይህ ጥቃት እንዲቆም የጣሊያን ሰላቶንና ባንዳን የመመከት ብሎም አሳፍሮ የመመለስ የድል ባህል ያለው አማራ የሆነ ሁሉ በየአካባቢው በመደራጀት ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠትና መመከት ይጠበቅበታል ነው ያለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply