አማራ ሰፊ አገር እንጅ  ክልል ከልሎት አይኖርም! – በላይነህ አባተ

የአማራ ክልል እየጮህ፣ ጋዜጠኛ ነኝ የምትል ለንጨጫም፤ አማራ በአንተ ላንቃ እንጅ፣ ክልል ኖሮትም አያውቅም፡፡ ቁማር የሚጫወቱብህ፣ ባንዳው ገረዱ ብአዴን፤ የተንኮል ቁማርተኞቹ፣ ከብት መስሏቸው ልክ አንተን፤ ክልልህ ግባ እያሉ፣ በሜንጫ አረዱት አማራን፡፡ አማራ ነፃ ሕዝብ እንጅ፣ የእንሰሳ መንጋ አይደለም፤ እንደ ከበት በክልል ታስሮ፣ ሳር ቅጠል ሲነጭ አይኖርም፡፡ አማራ እንደ  አንበሶቹ፣ እንደ አያቶቹ በርትቶ፤ በመላ እርስቱ ይኖራል፣ ሰው አራጅ አውሬን ድል ነስቶ፡፡ የመላ ጦቢያ አፈሩ፣ ውሀው አየሩ ይመርመር፤ በአማራዎች  ሥጋ ደም፣ በአጥንቶቻቸውም ተከብሯል፡፡ ሙቱን ብአዴን ካርታ አርገው፤ የተንኮል ቁማር ቢሰሩም፣ አማራና ጪስ መውጫ በር፣ ጎዳናው ጠፍቶት አያውቅም፡፡ ለይህ አድግ ተንኮል ገብረህ፣ የአማራ ክልል የምትል፤ እንደ ብአዴን ካድሬዎች፣ የምትሸጥ ያያትህን ክብር፤ በታረደችው እርጉዝ

Source: Link to the Post

Leave a Reply