አሜሪካ ለሕዳሴው ግድብ አዲስ የስምምነት ስነድ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላት ተሰማ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/200270

የአፍሪቃ ህብረት አደራዳሪ እንዲሆን በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት አለ

ዋዜማ ራዲዮ– የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ በተካረረበት በዚህ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ሀገራቱን ለማስማማት አዲስ የስምምነት ስነድ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላት ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
የዓለም ባንክና ዩናይትድ ስቴትስ ላለፉት ሁለት ወራት በታዛቢነት ሲከታተሉት የነበረው የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ሊፈታ ባለመቻሉ የየሀገራቱ ባለስልጣናት ዋሽንግተን ላይ ለውይይት ታድመዋል።
የዋሽንግተኑ ስብሰባ ዓላማ እስካሁን የተደረጉ አራት ስብሰባዎችን ውጤት ለመነጋገር ቢሆንም በአሜሪካ በኩል ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን የሚፈቱበትን መንገድ ያካተተ አዲስ የስምምነት ሰነድ ሀገራቱ እንዲፈርሙና ድርድሩ እንዲቀጥል የሚል ፍላጎት አላት።
የድርድሩን ጊዜ ማራዘም የሚል ሀሳብም አማራጭ አንደሆነ ስምተናል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሀ አሞላል እንዲሁም በግድቡ የላይኛውና የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ድርቅ ቢከሰት እንዴት መቋቋም ይቻላል በሚለው ላይ በኢትዮጵያ ; ግብጽና ሱዳን በካይሮና በካርቱም አንድ አንድ ጊዜ እንዲሁም በአዲስ አበባ ደግሞ ሁለት ጊዜ በውሀ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው እየተመሩ ያደረጉት የቴክኒክ ስብሰባ ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል። በአሜሪካ ጠሪነት በተጀመረው ይህ ስብሰባ ተጨማሪ ሁለት የዋሽንግተን ስብሰባዎችም ይደረጉበታል የሚል ስምምነት የነበረው ነው። አለም ባንክና አሜሪካም የውይይቱ ታዛቢ እንደሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በዋሽንግተን የሚደጉት ሁለት ስብሰባዎች የቴክኒክ ሳይሆኑ በሶስቱ ሀገራት የሚደረጉ ውይይቶች ሪፖርት ይቀርብበታል የተባለ ሲሆን አንዱ የዋሽንግተን ስብሰባ ታህሳስ ወር ተካሂዷል።ሁለተኛው የዋሽንግተን ስብሰባም ዛሬ ይጀመራል።ይህ ስብሰባ አራቱ ቴክኒካዊ ስብሰባዎች ከምን እንደደረሱ ለመነጋገር እንጂ ቴክኒካዊ እንዳልሆነ ተሰምቷል።
አሜሪካ ግን በዚህኛው የዋሽንግተን የህዳሴው ግድብ ስብሰባ ላይ ስምምነት የማፈራረም ፍላጎት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.