አሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኗ በየመን ተመትቶ መውደቁን አረጋገጠች

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%88%B0%E1%8B%8D-%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%89%A3-%E1%8A%A0%E1%8B%8D%E1%88%AE%E1%8D%95%E1%88%8B%E1%8A%97-%E1%89%A0%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%95-%E1%89%B0%E1%88%98/

አዲስ አበባ፣ነሃሴ 16፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል ንብረትነቱ አሜሪካ የሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን በየመን ተመትቶ መውደቁን አስታውቋል ።

ኤም ኪው-9 የተሰኘው አሜሪካ ሰራሹ ዘመናዊ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ትናንት በየመን በሀውቲ ታጠቂዎች በሚሳኤል ተመቶ መውደቁ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎም የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል ከድርጊቱ ጀርባ ያለውን አካል ለማወቅ ምርመራ  እያካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ከድርጊቱ ጀርባ  የሀውቲ  ታጣቂዎችን የምትደግፈው ኢራን ልትኖር እንደምትችል ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሰኔ ወር  ላይ ኢራን  በህገ ወጥ መንገድ  በሀገሪቱ የአየር ክልል በመግባት  ቅኝት ስታደርግ ነበር ያለቻትን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏ ይታወሳል ።

በትናንትናው ዕለት  በየመን በሀውቲ ታጠቂዎች በሚሳኤል ተመቶ የወደቀው የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ሁለተኛው መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ ፦www.presstv.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.