አሜሪካ በሶማሊያ በፈፀመችው የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%89%A0%E1%88%B6%E1%88%9B%E1%88%8A%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8D%88%E1%8D%80%E1%88%98%E1%89%BD%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%8B%E1%8B%AD/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሶማሊያ በፈፀመችው የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ ።

እንደ አፈሪኮም ገለፃ ፥ወታደሮች በአልሸባብ ላይ በወሰዱት የአየር ላይ ጥቃት ሁለት የአልሸባብ ታጣቂዎችን የተገደሉ ሲሆን ፥አንድ የቡድኑ መኪናም እርምጃ ተወስዶበታል።

የተወሰደው የአየር ላይ ጥቃትም በነዋሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሱ ተገልጿል።

ይህ ስኬታማ ዘመቻ  የሶማሊያ መንግስት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ቡድኖችን ለማጥፋት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበረታታ ነው ተብሏል።

ጥቃቱ ቡድኑ ወደ ፊት በአካባቢው ለመፈፀም ያቀደባቸውን ቦታዎች ለማጥናት፣የአመራር ኔትወርኩን ለመበጣጠስና በቀጠናው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል መሆኑን በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ (አፍሪኮም) አስታውቋል።

አልሸባብ በደቡብና ማዕከላዊ ሶማሊያ ግዛቶች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ከመሆኑም በላይ ለተጎጅዎች የሚደረግን ሰብዓዊ ዕርዳታ በማስተጓጎል ላይ መሆኑ በመግለጫው ተጠቁሟል።

የሽብር ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድም ከሀገሪቱ መንግስትና ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አፍሪኮም አስታውቋል።

አልሸባብ በሶማሊያ የራሱን መንግስት ለመመስረት በፈፀመው ጥቃት፥ እስካሁን በርካታ ዜጎች የሞቱ ሲሆን በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከሞኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

Share this post

One thought on “አሜሪካ በሶማሊያ በፈፀመችው የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.