አሜሪካ በከባድ የአውሎንፋስ ስጋት ውስጥ ትገኛለች

Source: https://fanabc.com/2018/09/%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%89%A0%E1%8A%A8%E1%89%A3%E1%8B%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%8D%E1%88%8E%E1%8A%95%E1%8D%8B%E1%88%B5-%E1%88%B5%E1%8C%8B%E1%89%B5-%E1%8B%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዩናይትድ ስቴትስ በከባድ አውሎንፋስ ስጋት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሰሜን ካሮላይና ግዛት እንደሚደርስ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ይህ ፍሎረንስ በመባል የሚጠራው አውሎንፋስ በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር ይጓዛል ተብሏል፡፡

የግዛቱ ባለስልጣናት ከኃይል መቆራረጥ በተጨማሪ የሰው ህይወት ሊጠፋ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

የፍሎረንስ የመጀመሪያ ተጠቂ ሰሜን ካሮላይና እንደምትሆን የሚጠበቅ ሲሆን ከወዲሁ በከባድ ውሽንፍርና ጎርፍ ተጠቅታለች፡፡

የሀገሪቱ የአየርንብረት ትንበያ ኃላፊ ሰሜን ካሮላይና በስምንት ወራት የምታገኘውን ዝናብ በሁለትና በሦስት ቀናት ውስጥ እንደሚያጋጥማትም ገልጸዋል፡፡

በሚሊየን የሚቆጠሩ የካሮላይና እና የቨርጂኒያ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ተላልፎላቸዋል፡፡

ከ12 ሺህ በላይ የሚልቁ ሰዎችም መጠለያዎች ውስጥ መግባታቸውም ተነግሯል፡፡

የግዛቱ ባለስልጣናት ከኃይል መቆራረጥ በተጨማሪ የሰው ህይወት ሊጠፋ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.