አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ያሰማራቻቸውን ወታደሮች ልታስወጣ ነው መባሏል አስተባበለች

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%89%A0%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%8A%AE%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%8B%AB%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%88%AB%E1%89%BB%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%89%B3/

አዲስ አበበ፣ ህዳር 11፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ያሰማራቻቸውን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከሀገሪቱ ልታስወጣ ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ አስተባብላለች።

ቾሰን ኢልቦ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ጋዜጣ አሜሪካ በሳኦል ያሰማራቻቸውን 4ሺህ የሚደርሱ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከሀገሪቱ ልታስወጣ መሆኑን በትናንታው ዕለት መዘገቡ ይታወቃል።

ለዚህም በደቡብ ኮሪያ የተሰማሩት የዩናይትድ ስቴትስ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች አሜሪካን ለከፈተኛ ወጪ እየዳረጓት መሆኑ በምክንያነትነት ጠቅሷል ።

ይህን ተከትሎም የአሜሪካ መካላከያ  ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ጋዜጣው መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ ያሰማራቻቸውን ወታደሮች ልታስወጣ ነው በሚል የተሰራጨው ዘገባ መሰረተ ቢስ መሆኑን  አስታውቋል።

አሜሪካ በኮሪያ ልሳነ ምድር  ያሰማራቻቸውን የሰላም አስከባሪ ወታደሮች የማስወጣት ዕቅድ የሌላት መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

ፔንታጎን ቾሰን ኢልቦ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ጋዜጣ ያሰራጨውን ዘገባም ሃላፊነት የጎደለው  መሰረተ ቢው ውንጀላ  ሲል አጣጥሎታል ።

አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1950 እስከ1953 የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በቀጠናው ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ማሰማራት መጀመሯ ይታወሳል ።

አሁን ላይም 28 ሺህ 500 የሚደርሱ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን በኮሪያ ልሳነ ምድር ያሰማራች መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ ፦ሬውተርስ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.