አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አቀረቡ

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%88%B3%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%88%AC%E1%8B%B5%E1%8B%8B%E1%8A%95-%E1%88%81%E1%88%B4%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%88%B9%E1%88%98%E1%89%B5-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%8B%B3%E1%89%A4/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በኤርትራ የኢፌዴሪ አምሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው ዕለት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀረቡ፡፡

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት አምሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሀምሌ ወር 2010 ዓ.ም ላይ መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከ20 ዓመታት በኋላ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን ተከትሎ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን ይታወሳል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ቀደም ሲል በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡

Share this post

One thought on “አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አቀረቡ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.