አርሰን ቬንገር ወደ እግር ኳሱ ዓለም ሊመለሱ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%88%B0%E1%8A%95-%E1%8B%8C%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%88%AD-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%8A%B3%E1%88%B1-%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%88%8A%E1%88%98%E1%88%88/

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር አዲስ ሚና ይዘው ወደ እግር ኳሱ እንደሚመለሱ አስታወቁ፡፡

22 ዓመታትን በአርሰናል የቆዩትና በፈረንጆቹ 2017-2018 የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር የተለያዩት ቬንገር ወደ እግር ኳሱ ዓለም እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።

ቬንገር በንግግራቸው ወደ እግር ኳሱ ዓለም ቢመለሱም ወደ አሰልጣኝነቱ ላይመለሱ እንደሚችሉ ነው ፍንጭ የሰጡት፡፡

አርሰን ቬንገር በስፖርቱ ዓለም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከተሰማራ ኩባንያ ጋር ድርሻ ገዝተው በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ቬንገር በኩባንያው ድርሻ እንደሚኖራቸውና በአማካሪነት እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያው ቬንገር በንግድ እና በምርት ልማት ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው የገለጸ ሲሆን፥ በተጫዋቾች የቴክኒካል፣ ታክቲካል እና አካላዊ ብቃት ላይ ሙያዊ ትንተና ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

ይህም አርሰን ቬንገር በእግር ኳስ ያላቸውን ተሳትፎ እንደማያቋርጠውም ገልጿል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.