አርበኞች ግንቦት ሰባት የተሰኘው ድርጅት በዐማራ ሕዝብ ቁስል ላይ ጨው ነሰነሰ! ውግዝ ከማርዮስ! – ሞረሽ ወገኔ

Source: http://welkait.com/?p=12084
Print Friendly, PDF & Email

አርበኞች ግንቦት ሰባት የተሰኘው ድርጅት በዐማራ ሕዝብ ቁስል ላይ ጨው ነሰነሰ!  ውግዝ ከማርዮስ! ከግንቦት ሰባት ጋር ያበረ ዐማራ ጥቁር ውሻ ይውለድ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ጥር ፳፰ቀን ፪ሺህ፲ዓ.ም. ቅጽ ፮ቁጥር ፭

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ግንቦት 7 የተሰኘው ድርጅት ከትግሬ-ወያኔ የከፋ የዐማራ ሕዝብ ጠላት መሆኑን ከሚያራምደው ዓላማና ከሚፈጽማቸው ፀረ-ዐማራ ተግባሮች ተነስተን «ለጥቃታችን መከታ ያልሆነን ድርጅት፣ ለመሞቻችን ምክንያት አይሁን» በሚል ርዕስ መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን መግለጫ ያዩ የድርጅቱ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጀሌዎች «እንዴት ሆኖ፣ ግንቦት 7 የዐማራ ጠላት ይሆናል? ድርጅቱ ካሉት አባላት ከመቶ ሰማኒያ ምናምኑ ያህል ዐማራዎች ናቸው» በማለት ቡራ ከረዩ ማለታቸውን እናስታውሳለን። «ዕውነትና ንጋት እያደር ይፈካል» እንዲሉ፣ እኛ ያልነው ዕውነት፣ ደጋፊዎቹ የጮኹበት ውሸት መሆኑን ሰሞኑን ድርጅቱ፣ «ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» ጋር በመሆን፣«ከአርበኞች ግንቦት ሰባትና ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ» በሚል ርዕስ ባወጣው ሀተታ ፀረ-ዐማራነቱን ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል። ከዚህ ፀረ-ዐማራና የትግሬ-ወያኔ ዓላማ አራማጅ ከሆነ ድርጅት ጋር የቆመ የዐማራ ልጅ፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የክሕነት ሥልጣን ባይኖረውም ፣እንደባህላችን፣ ወግድ ይሁዳ! ውግዝ ከማርዮስ፣ ጥቁር ውሻ ውለድ እንድንል፣ በዕውቀታችሁ፣ በጊዜአችሁና በገንዘባችሁ ያሳደጋችሁት ድርጅት በዐማራው ቁስል ላይ የነሰነሰው ጨው አስገድዶናል። «ቀጣፊን ሲረቱ፣ በወንድሙ በእህቱ» እንዲሉ፣ የግንቦት 7 ቃል አቀባይ የሆኑት የኢሣት ሠራቶች ጭምር መግለጫው ተገቢና ትክክል አለመሆኑን በየገጸመጽሐፋቸው ገልጸዋል።የድርጅቱን የሕዝብ ግንኙነት ተግባርም አውግዘዋል።

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) አመሠራረትና ተልዕኮ በሚገባ የተከታተሉ ወገኖች የሚያምኑትና የሚገባቸው፣ ትሕዴን፣ ወያኔ በሕዝብ ግፊት ከሥልጣን ቢወገድ፣ አሁን ግንቦት 7 እንደሚለን በሰው ደም ፣ከሁሉም በላይ በዐማራ ደም የተጨማለቁ የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ ምንም ዓይነት ተጠየቅ እንዳይደርስባቸው ዘብ እንዲሆን፣ ከቻለም የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን፣ በሻዕቢያና በትግሬ-ወያኔ ትብብር የተመሠረተ ድርጅት መሆኑን ያውቃሉ። ይህን ለመረዳት ከማንም የተሻለ የግንቦት 7 አመራር ከነመለስ ጋር በነበረው ጥብቅ ግንኙነትና አሁንም ከሻዕቢያ ጋር ባለው ግንኙነት ከማንም የተሻለው ዕውቀቱም ሆነ ግንዛቤው ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል። ሞላ አስገዶም የትሕዴን መሪ፣ ብርሃኑ ምክትል አድርጎ፣ የመድው ሰው ፣የሁለቱ ድርጅቶች የስምምነት ሰነድ የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ከነሠራዊቱ ከድቶ አዲስ አበባ መግባትና፣ በግንቦት 7 አባላትና አካላት ላይ ያሳደረው የኅሊና ስብራት የቱን ያህል እንደሆነ የሚያውቁ ያውቁታል። ግንቦት 7 እና አመራሩ ይህን መራራ ሐቅ ወደ ጎን ገፍውና አራሙቻ ጭነው፣ዛሬም አንድ ነን በማለት በዐማራው ቁስል ላይ ጨው መነስነሱን ሥራዬ ብለው ይዘውታል። ሁለቱን ድርጅቶች እንዲህ አንድም ሁለትም ያደረጋቸው መሠረታዊ ምክንያቱ ፀረ-ዐማራ አቋማቸውና አመለካከታቸው እንደሆነ ተግባራቸው በግልጽ ያሳያል። ….. (Read more, pdf)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.