አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ጎንደር ዞን በአገዛዙ ላይ ባደረስኩት ጥቃት 9 ታጣቂዎችን ገደልኩ አለ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/43839

አባይ ሚዲያ ዜና

በአሰግድ ታመነ

አርበኞች ግንቦት 7 ሚያዝያ 07 ቀን 2010 ዓ / ም  በሰሜን ጎንደር ዞን በመንቀሳቀስ በሕዝብ ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን የአገዛዙ መከላከያ አባላት አንድ ቲም ላይ በወሰድኩት እርምጃ ዘጠኝ/9/ ወታደሮች  መግደሉን አስታውቆ 8 ወታደሮችን ማቁሰሉ ዘግባል።

የሟቾቹ አስከሬን ጎንደር አዘዞ ወደ ሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ የገባ ሲሆን የአንዳዶቹ አስከሪን ወደ ትውልድ ቦታቸው እየተወሰደ እንደሆነ አያይዞ ዘግቧል።

በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ሆስፒታል በርካታ ወታደሮችና በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መሞላቱ የተነገረ ሲሆን በአካበቢው ያለው ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነና ግርግር እንደሚታይ የአይን እማኞች ገልፀዋል።

በምሽቱ በነበረው ውጊያ የተገደለ አንድ አመራር አስከሬኑ ዛሬ ሚያዚያ 08 ቀን 2010 ዓ / ም ረፋድ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ተጭኖ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ ስርሀተ ቀብሩ ተፈፅማል ተብላል።

 

Share this post

2 thoughts on “አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ጎንደር ዞን በአገዛዙ ላይ ባደረስኩት ጥቃት 9 ታጣቂዎችን ገደልኩ አለ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.